Aba Selama: ማህበረ ቅዱሳንና ሰለፊያ!! ግልባጩ ማነው? - - - Read PDF:
ከአውደ ምሕረት የተወሰደ የማህበረ ቅዱሳን ሰለባ የሆኑ ብዙ የቤተክርስቲያን አባቶችና ልጆች ማቅን በአሸባሪነት
ከፈረጁት ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆንም፣ ማቅ ግን እንዲህ የሚሉኝ ለቤተ ክርስቲያን ጥብቅና ስለቆምኩ ነው በሚል ራ...
ይድረስ ለአባ ሰላማዎች
ሰሞኑን
በተወካዮች ምክር ቤት የተወራው ወሬ ጮቤ ያስረገጣችሁ ይመስላል፡፡ ለደስታችሁ ወደር ለመድረሻችሁም ድንበር
እንደማይገኝለት ግልጥ ነው፡፡ ምክንያቱም የምትጠሉት ማህበር፣የሚያንገሸግሻችሁ ማህበር፣መግቢያ መውጫ ያሳጣችሁ
ማህበር፣ የስርቆትን በር የዘጋባችሁ ማህበር፣ከአባቶቻችሁ የተላካችሁትን እንዳታስፈጽሙ ጋሬጣ የሆነባችሁ እግር በግር
እየተከታተለ ሥራችሁንና ማንነታችሁን የሚያሳብቅባችሁ ማህበር በአንድ በተከበሩ ሰው ያውም ለኛ ብቻ ሳይሆን ለዓለም
ስጋትና ጭንቀት ከሆነው ውሃቢዝም ጋር አጣግተው አክራሪ የሚል ቃል ስለተናገሩላችሁ እግራችሁ ከመሬት ከፍ ብሎ
ጭንቅላታችሁ ከሰማይ እስኪላተም ድረስ አዘለላችሁ አስፈነደቃችሁ፡፡ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡
የሆነ
ሆኖ ጠቅላይ ሚኒሰትራችን ማህበረ ቅዱሳንን ከንደዚህ አይነት አክራሪና አሸባሪ ቡድን ጋር ማነፃፀራቸው ወይ
የራሳቸው ችግር አልያም መረጃውን የሰጣቸው አካል ችግር ይሆናል፡፡ ምክንያቱም መረጃ እንጂ ማስረጃ የላቸውማ፡፡
ምናልባት መረጃውን ከናንተ ሳይቀበሉት አይቀሩም እንድል አድርጎኛል ምክንያቱም እናንተጋ ያለው መረጃ ጥላቻ እንጂ
ሌላ አይደለምና፡፡ ለምን ብትሉኝ ማህበረ ቅዱሳን በክፉ በተነሳ ቁጥር/በናንተና መሰሎቻችሁ/ ከበሮ ይዛችሁ እንቢልታ
እየነፋችሁ ትጋልባላችሁ ወይም ትፈነጥዛላችሁ፡፡ ለምን ብዬ አልጠይቃችሁም መልሱን አውቀዋለሁና፡፡ እናንተና ማህበረ
ቅዱሳን እኮ በግና ፍየል ናችሁ፡፡ ግብራችሁና አፈጣጠራችሁም አይስማማም እነርሱ ስለማነፅ ሲያስቡ እናንተ
ስለማፍረስ በቃ ግብራችሁ ይሄ ነው፡፡ ማፍረስ፡፡
የማህበረ
ቅዱሳን ዓላማና ግብ ምን እነደሆነ ለእውነተኞች የተዋህዶ ልጆች የተሰወረ አይደለም፡፡ሥራቸው ግልጥ ውጤቱም የሚታይ
ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለናንተና ባልንጀሮቻችሁ መራራ እንጂ የሚጣፍጥ እንደማይሆን ይታወቃል፡፡ እነሱን እግዚአብሔር
ለወቅቱ የቤተክርስቲያናችን ፈተናዎች የአባቶቻቸውን ዱካ ተከትለው መንፈሳዊውንም ቁሳዊውንም ቅርስ እየጠበቁና
እያስጠበቁ እንዲያቆዩልን ያስነሳቸው መንፈሳውያን አገልጋዮች ናቸው፡፡
ይሁንና
ለናንተም ሆነ ለመንግሳታችን የማይዋጥ ሃቅ እንዳለ መደበቅ የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ይኸውም ባሰባችሁትና ባቀዳችሁት
መንገድ ቤተክርስቲያኗ አልተበታተነችም፣ፕሮቴስታንትም አልሆነችም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ክርስቶስ በደሙ
የመሰረታት፣ሐዋርያት የሰበኳት፣ሰማዕታት ያፀኗት በመሆኗ ነው፡፡ እንጂማ እንደናንት በኮሚቴና በካርድ የተመሰረተች
ብትሆን ኖሮ ይህን ዘመን ባላገኘናት ነበር፡፡ አሁን ደግሞ አባታቶቻችን ዝም ቢሉም እያዩ እንዳላዩ ቢሆኑም ለነሱ
መንቃት ይሆን ዘንድ ማህበረ ቅዱሳን ከ20 ዓመታት በፊት በእግዚአብሔር ፈቃድ በብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ
3ኛ ቡራኬና ምክር ተመስርቶ ይሄው ዛሬ መላው የተዋህዶ ልጆችን በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩትን
በጊቢ ጉባዔ በማስተማር ተምረው የጨረሱትን ደግሞ አባል በማድረግ በመንፈሳዊውም በዓለማዊውም በቂ እውቀት ይዘው
እንዲወጡና በሥነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸው ሆነው ብቁ አገልጋይ እንዲሆኑ እያደረገ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ በሰበካ
ጉባዔ በመመዝገብ የድርሻቸውን እየተወጡ በሰንበት ትምህርት ቤቶችና በስብከተ ወንጌል አገልግሎትም እየተጉ
ተልእኮአቸውን በተገቢው መንግድ እየተወጡ ናቸው፡፡ ለናንተም የእግር ብረር ሆነውባችሁ ይታያሉ፡፡ ይህ ደግሞ
ባያስደስታችሁ አይፈረድባችሁም እነሱ እውነተኞች እናንት ደግሞ እኩይ ዓላማ ስላላችሁ እነሱ ይጠብቃሉ እናንት
ትሰርቃላችሁ፡፡ እነሱ ሙዳዩን ይሞላሉ እናንተ ደግሞ ትገለብጣላችሁ፡፡ እነሱ ያሬዳዊ ዜማን ያስተምራሉ እናንተ ደግሞ
ዘፈን ቢዘፈንስ ዜማን የወሰነ ማነው ትላላችሁ/መጋቢት 11 አና 12/04 ዓ.ም በደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍና
ቅዱስ ሚካኤል ሰባኬ ወንጌል ጉባዔ ላይ የተነገረ/ እነርሱ ነጠላ በመስቀል ምልክት አጣፍተው ዝቅ ብለው ያገለግላሉ
እናንተ ደግሞ ሳይገባችሁ ሰናፊል ለብሳችሁ መስቀል አንጠልጥላችሁ እዩኝ እዩኝ ትላላችሁ፡፡
ስለዚህ
አባ ሰላማዎች እጃችሁን ከቤተክርስቲያን ላይ አንሱ ባትችሉ ደግሞ እግዚአብሔር ጊዜ አለውና እንጠብቃለን፡፡ መቼም
እኛ ሰይፍ አናነሳም ሰይፍን የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ ብሎ ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡
የያዛችሁት አካሄድ ግን አያዋጣችሁም፡፡ በአንድም በሌላም መንገድ ምንፍቅናን መስበክ ሥራችሁ እነደመሆኑ ይህንን
የሚቃወማችሁን ማህበረ ቅዱሳንን መሳደብ ላይ ታተኩራላችሁ፡፡ ይህ ደግሞ ወለል ያለ እውነት ነው፡፡ እናንተ
ገድላት፣አዋልዕድ መጻሕፍት እና ቅዱሳን አያስፈልጉም ትላላችሁ፤ ስለዚህ እናንት ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን ጥብቅና የመቆም መብቱም ሞራሉም አይኖራችሁም፡፡ ስለዚህም ዞር በሉ፡፡ ተሃድሶዎች ናችሁ፡፡
ተላላኪዎች፡፡
በመጨረሻም
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩም ቢሆኑ ምን እንደነካቸው እንጃ ያዩበት መነፅር ያሳያቸው የማህበረ ቅዱሳንን አክራሪ መሆን
ነው፡፡ እሳቸው ከመሰላቸው መሰላቸው መነፅራቸው ግን አሳስቷቸዋል፡፡ የማይነፃፀር ሁለት ነገር አነፃፅረዋል
ውሃቢዝምንና ማህበረ ቅዱሳንን፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ግብር አትክፈሉ ብሏል እንዴ? ኮርቶዶክሳዊ መንግስት ይቋቋም ብሏል
እንዴ? ሌላ ሃይማኖት በኢትዮጵያ መኖር የለበትም ብሏል እንዴ? ነገር ግን በተጨባጭ መረጃ በቁጥር እንበልጣለን
ብሏል፡፡ እውነት ነው፡፡
ሌላው
በየትኛውም የሃይማኖት ክብረ በዓል ላይ የማህበረ ቅዱሳን አባላት ጥቅስ ወይም መፈክር ያለበት ካኔቴራ ለብሰውም
አስለብሰውም አያውቁም፡፡ ይልቅስ እንደሃይማኖታቸው ትምህርትና እንደሃገራቸው ባህል ነጭ በነጭ ይለብሳሉ እንጂ፡፡
ጥቅስ በካኔቴራቸው ላይ ጻፉ የተባሉትም ቢሆኑ የቤተክርስቲያን ልጆች እንደመሆናቸው ይህንን ጥቅስ ተጠቅመውበታል፡፡
እኔም በዚህ ላብቃ “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፣4፡፡ይህ ደግሞ የሃይማኖታችን አስተምህሮ እንጂ ማህበረ ቅዱሳን ከራሱ ያፈለቀው ጥቅስ አይደለም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን በረከታቸው አይለየን አሜን፡፡
Amen
ReplyDeleteTekekel new