Thursday, May 17, 2012

አሠርቱ ትዕዛዛት-ክፍል ፪


በስመ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ሐዱ ምላክ ሜን፡፡

‹‹ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። ››
ንዳንዶች ይህን ሕግ ሲያነቡ ወይም ሲሰሙ የሚመለከታቸው ከሐድያን መናፍቃን ወይም ብዙ በመመራመር ወይም ከመፈላሰፍ የተነሳ ከሃይማኖት የወጡትን ነው ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም ንጾማለን፣ ሥራት ናወጣለን፣ ዘወትር ንጸልያለን፣ ከልባችን ንዘምራለን፣ በቤተ ክርስቲያን የጸሎት ምልኮትና የመዝሙር መርሐ ግብሮችም ተሳትፎ ናደርጋለንና ዛዙ ኛን ይመለከተንም ብለው የሚሠሩትን የሚታየውን ስለሚያስቡ ይሆናል፡፡  ነገር ግን ይህ ዛዝ ማንንም ሳይለይ ሁሉንም ሰው የሚመለከት ነው፡፡ ሌሎች ማልክት የተባሉትም ከድንጋይ ተጠርበው ንጨት ለዝበው የተሠሩትን ታት፣ በፀሐይ፣ በጨረቃ፣ በከዋክብት ማምለክን ብቻ ሳይሆን ያንዳንዱ ሰው የሚያመልከውን የየራሱን ታት ናቸው፡፡

በጥንት ዘመን ንዳንድ ሰዎች ከፍርሃት ወይም ከበዛ የሥጋቸው መሻት ወይም በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ንግዳ  ማልክትን ያመልኩ ነበር፡፡ ‹‹የእስራኤልም ልጆች በከነዓናውያን በኬጢያውያንም በአሞራውያንም በፌርዛውያንም በኤዊያውያንም በኢያቡሳውያንም መካከል ተቀመጡ። ሴት ልጆቻቸውንም አገቡአቸው፥ እነርሱም ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆቻቸው ሰጡ፥ አማልክቶቻቸውንም አመለኩ። የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር አደረጉ፥ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተው በኣሊምንና አስታሮትን አመለኩ። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ በመስጴጦምያ ንጉሥ በኵሰርሰቴም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው የእስራኤልም ልጆች ለኵሰርሰቴም ስምንት ዓመት ተገዙለት።›› መሳ 36-14፡፡ እንደተባለ የመልካምና የክፉ አማልክት ነበሩአቸው፡፡ አታምልኩአቸው የተባሉ ቢሆኑም ሰዎች የሚያመልኳቸውን ጥቂቶቹን እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡
1. ገንዘብን ማምለክ
ገንዘብ ሰዎች ያመለኩት የእግዚአብሔርንም አምላክነት የሚቀናቀን ጣዖት ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን በመዋዕለ ሥጋዌው ‹‹ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።›› ማቴ 624 እንዳለን፡፡  እግዚአብሔርን አምናለሁ እያለ ገንዘብንም ከልክ በላይ የሚወድ ራሱን ያስታል፡፡ ገንዘብን በማከማቸት ከመጠቀም ይልቅ የሚደሰቱበት ካሉ ገንዘብን ያመለኩ ናቸው፡፡ ገንዘብ ሲገባ ሲደሰቱ ሲወጣ ደግሞ በስለት የተቆረጡ ያህል የሚሰማቸውም ምንም ማውጣት/መለገስ/መመጽወት የማይሹ በፍቅረ ንዋይ የተቃጠሉ ጌታችን ‹‹ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፡፡›› ማቴ 619 ያለንን የዘነጉ ናቸው፡፡  ወገኖቼ የገንዘብ ፍቅር ወደ ልባችን ገብቶ እንዲገዛን አንፍቀድለት፡፡ የገንዘብ መጠናችንም እየጨመረ ሲሄድ መልካም የሆነ ሥራን (ንግድን፣ፕሮጀክቶችን) በማቀድና በመሥራት አንድ ቅዱስ አባት ለአንድ መንፈሳዊ አባት ‹‹ገንዘብ ካለህ በሥራ ላይ አውለው ከሌለህም ምንም አትሰብስብ›› እንዳሉት እንጠቀምበት፡፡
2. መልካም ያደረጉልን ወይም ውለታ የዋሉልንን ማምለክ
በርካታ ሰዎች ውለታ የዋሉላቸውን ሰዎች ያመልካሉ እንዲህ ያሉትንም ሰዎች ከማስከፋት እግዚአብሔር ቢቀየማቸው ይመርጣሉ፡፡  እኛ ለሰዎች መልካም ነገርን የምናደርገው በነርሱ ዘንድ ለመመለክ ወይም የነርሱ ገዢዎች ለመሆን መሆን አይገባውም፡፡  መልካም ያደረጉልን ወይም ያገዙንን ሰዎች የምናመልካቸው ከሆንን በነርሱም ላይ የሚናገር ማንኛውም ሰው ቢኖር የተነገረው ትክክል ቢሆንም ስለ ስህተታቸው የምንከራከርላቸው ሆነን እንገኛለን፡፡ ይህም የማይገባ መሆኑን ‹‹ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ›› ያለ እግዚአብሔር ያዘናል፡፡  ሰዎች ለመልካም ሥራቸው ሰማያዊ ዋጋ ከእግዚአብሔር ዘንድ ማግኘት ሲገባቸው እኛ በሙገሳ ብዛት እንዳያስቡት የምናደርግና ዋጋቸውንም የምናሳጣቸው መሆን አይገባንም፡፡
3. ዝናን ማምለክ
አንዳንድ ሰዎች ለራሳቸው ወይም ለሚያውቁት ሰው ዝና ሲሟገቱ ይገኛሉ፡፡ ስህተታቸውንም በመሸፈን ቤተ ክርስቲያንንም ሳይቀር ስለራሳቸው ክብርና ዝና መጠበቅ ሲሉ ይከሳሉ እውነትንም ይደብቃሉ፡፡ ይህም ለዝና መገዛትና ዝናን ማምለክ ነው፡፡ በባዶነታችን ላይ የሌለንን ዝና ጨምሮ የሚሟገትልን አጥፊአችን ነው፡፡ በመጨረሻ ከውድቀታችን ሊያተርፈንም አይችልም፡፡  ስለ ሰው ዝና ሲባል እውነትን መሥዋዕት ማድረግ ለሐሰትም መሟገት አይገባም፡፡ ‹‹ኀጥኡን የሚያጸድቅና በጻድቁ ላይ የሚፈርድ፥ ሁለቱ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው።›› ምሳ 1715፡፡ እንዳለን፡፡
ለእግዚአብሔር የሚገባውን የሚገባ ክብር ለሰው የሚሰጥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰውን ያመልካል፡፡ እግዚአብሔርን ደስ ከማሰኘት ይልቅ ሰውን በማይገባ ነገር የሚያስደስት፣ እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ይልቅ ለሰው አላግባብ የሚታዘዝ የታዘዘለትን እርሱን ያመልካል፡፡ ‹‹ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም።›› ገላ 110፡፡ እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ፡፡  ማንኛውም ሰው የሚያደርገውን ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት በንጹሕ አእምሮ ማድረግ ይኖርበታል፡፡  ሰው ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን ክብር፣ ፍቅርና አምልኮት ለማንም ሳይለውጥና ያላግባብም ማንንም ሳያወድስ፣ ለሌሎችም ዝና ሳያጎበድድ በተገቢው መንገድ መኖር አለበት፡፡
4. መሪዎችን ወይም ታላላቆን ማምለክ
ቅዱስ መጽሐፋችን ‹‹ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ።›› ዕብ 1317 በማለት የነገረን አታምጹባቸው ታዘዙአቸው ማለት እንጂ በእግዚአብሔር ፈንታ አምልኩአቸው ማለት አይደለም፡፡ መሪዎችም ሆኑ መንፈሳዊ አባቶች በሚገባቸው መጠንና ወሰን በመታዘዝ ልንገዛላቸው ከሚገባን በቀር ከእግዚአብሔር ጋር አወዳድረን ልናመልካቸውና ከእግዚአብሔርም የሚያጣላን ትእዛዝ በሚያዙን ጊዜ ይሁን ብለን ልንቀበላቸው አይገባንም፡፡  መሪ ወይም አባት ከሚገባው መንገድ የወጣ ከሆነ ከበታቹ ያለውም የግድ ተከትሎት እንዲሄድ አልታዘዘም፡፡ መንፈሳውያን መሪዎች (አባቶች) ከነበሩት አርዮስ ቄስ የነበረ ቢሆንም፣ ንስጥሮስ ጳጳስ የነበረ ቢሆንምከእውነት ባፈነገጡ ወይም በወጡ ጊዜ መንፈሳውያን ልጆቻቸው አስወግዘው ተለዩአቸው እንጂ ተከትለው አልሄዱም፡፡ ‹‹ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል፡፡›› የሐዋ. 529 ተብለናልና፡፡
ሰዎች መሪዎቻንን ወይም አባቶቻችንን ሊንታዘዝ ቢገባም የምንታዘዘው ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ማዕቀፍ ውስጥ መሆን ስለሚገባው ከእግዚአብሔር በላይ አድርገን አይደለም፡፡ ለእግዚአብሔር መታዘዛችን በምንም ምክንያት ለሰው በመታዘዝ መተካት አይገባውም፡፡ አንድ አባት ከእግዚአብሔር ጋር ሳይሆን ከራሱ ጋር ብቻ የሚያጣምረን ብቻ ከሆነ እውነተኛ አባት አይደለም፡፡ ኤፌ 61፡፡ ለመንፈሳውያን አባቶቻችንም ያለን መታዘዝ ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ የሚያወጣን ከሆነ መታዘዝ አይገባንም፡፡ ይህን ብናደርገውም ኃጢአት ነው፡፡ መታዘዝ ‹‹በጌታ›› ተብሎ ተጽፎልናልና፡፡ ‹‹ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።›› 1ኛ ዮሐ 41፡፡ እንዳለ መታዘዝ በመታወር ሳይሆን በመረዳትና በማስተዋል ነው፡፡
እግዚአብሔር የአብርሃምን ‹‹ይህ ከአንተ ይራቅ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ።›› ዘፍጥ 1825 በማለት የተናገረውን ቃሉን እንደተቀበለው፣ ሙሴም ‹‹ግብፃውያንስ። በተራራ መካከል ሊገድላቸው፥ ከምድርም ፊት ሊያጠፋቸው ለክፋት አወጣቸው ብለው ስለ ምን ይናገራሉ? ከመዓትህ ተመለስ፥ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ። ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘላለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን እስራኤልንም አስብ።›› ያለበት የምልጃ ቃሉን ተቀብሎ ‹‹እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው ክፋት ራራ።›› እንደተባለው ዘጸ 3212-14፡፡  መንፈሳዊ አባት የእግዚአብሔር መልእክተኛ በመሆኑ የመንፈሳዊ ልጁን ውስጣዊ ሰላም የሚያናጋ መንፈሳዊ ቅድስናውን የሚያፈርስና የሚፈታተን ትእዛዝ ማዘዝ የለበትም፡፡ ስለዚህ ታላቆችንና መሪዎችን በሚገባ መጠን መታዘዝ እንጂ ማምለክ ወይም ከፍርሃት የተነሳ ወደ አምልኮትም መሄድ አይገባም፡፡
5. ዓለምንና የዓለምን ፍላጎት ማምለክ
ዓለም ሌላኛዋ ጣዖት ናት፡፡ ዓለምን የሚወድ ለእግዚአብሔር መታዘዝ አይቻለውም፡፡ ‹‹አመንዝሮች ሆይ፥ ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።›› ያዕ 44 እንዲሁም ‹‹ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም። ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።›› ቀዳ ዮሐ 215-17፡፡ እንዳሉን፡፡ ሥልጣንን፣ ማዕረግን፣ ክብርን፣ ንብረትን ማምለክ ጣዖትን ማምለክ ነው፡፡
እግዚአብሔርን የምናመልክ ከሆንን ዓለምንና ፍላጎትዋን ድል መንሳት እንችላለን፡፡ ‹‹ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።›› 1ኛ ዮሐ 54 ፡፡ ዓለም ስታሸንፈን ደግሞ እምነታችን ፈጽሞ ይጠፋል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛል፡፡›› 2ኛ ጢሞ 410፡፡
ለምኞታቸው የሚገዙ እግዚአብሔርን በፍጹም ልባቸው፣ በፍጹም ሐሳባቸውና በፍጹም ኃይላቸው ማምለክ አይቻላቸውም፡፡  ውበታቸውንም የሚያመልኩ ስለርሱም ብቻ ሲናገሩ ሲተርኩ የሚውሉ ሲተረክላቸውም ደስ የሚላቸው አሉ፡፡  ‹‹ሆዳቸው አምላካቸው ነው፣ ክብራቸው በነውራቸው ነው፣ ሐሳባቸው ምድራዊ ነው›› ፊል 319 ሕይወታቸው መብልና መጠጥ(አረቄ፣አልኮል፣…) ብቻ የሆነ ይህንንም የሚያመልኩት አሉ፡፡ አዳምና ሔዋን የወደቁት ዘፍጥ 36 ኤሳው ብኩርናውን የሸጠው ዘፍጥ 2529-34፣ እስራኤልም ያጉረመረሙትና የተቀጡትም መብልን በመፈለጋቸውና በማምለካቸውም ነበር፡፡ ዘኁ 114-5፡፡
6. ራስን ማምለክ
ሌላኛው አደገኛ ጣዖት ራስን ማምለክ ነው፡፡ ከሥጋዊ ፍላጎት የተነሳ ራስን ከፍ ማድረግ፣ ሌሎችም እንዲያመልኩን እንዲያገኑንና እንዲፈሩን ማድረግ፣ መልካም የሆኑ ነገሮች በማንነታችን ውስጥ ተገኝተው እንዲያንቁንና እንዲፈሩን ማድረግ ራስን ማምለክ ነው፡፡  ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብን ያስገደለውን ሄሮድስን አደጋ ያመጣበት ችግር ውስጥም የገባው በትልም ተበልቶ ለመመሞት የደረሰው የማይገባውን ክብር ሲሰጡት ባለመቃወሙና የማይገባውን ክብር በመሻቱ ነበር፡፡ የሐዋ 1221-23፡፡  ሌሎችን ጣዖታት ድል ነስተው ራሳቸውን ግን ማሸነፍ የተሳናቸው ሄሮድስን የሚመስሉ ናቸው፡፡ ከራሳቸው በቀር ሌላ አስተዋይ፣ የሚሻል፣ ጠቢብ፣አለ ብለው ስለማያስቡ ራሳቸውን ያመልካሉ፡፡ ሰውም እንዲያመልካቸው ይሻሉ፡፡ ከራሳቸው በቀር ያለ ሁሉ
ስህተተኛ ነው፡፡
በዓለም ላይ ያሉ አምባ ጓሮዎች መነሻቸው ራስን ማምለክ ነው፡፡ ጌታችንም ይህን ከመሰለው እንቅፋት እንድንጠበቅ ‹‹በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ›› ማር 834 ያለን ከዚሁ ራስን የማምለክ ሕይወት እንድንጠበቅ ነው፡፡  ራስን መካድ ማለት ራስን እንደ ትቢያ በመቁጠር ‹‹እርሱ እግዚአብሔር ሊልቅ እኔ ላንስ ያስፈልጋል፡፡›› ዮሐ 330፡፡ ማለት ነው፡፡  ሳጥናኤልን ያዋረደው ራሱን የሁሉ የበላይ ለማድረግ መፈለጉ ነበር፡፡ ‹‹አንተን በልብህ። ወደ ሰምይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ። ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ።›› ኢሳ 1413-14፡፡  አሥራቱን በመክፈል ምትክ መውሰድ፣ ሰንበትን ለሥጋ ፈቃድ መፈጸሚያ ብቻ መጠቀም ራስን ማምለክ ነው፡፡ ፍላጎታችን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ሲጋጭ ፈቃዳችንን ከመፈጸም ይልቅ ራሳችንን በመካድ ለእግዚአብሔር እናስገዛ፡፡
7. ክህደት
ልበ አምላክ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ይላል።›› መዝ 131 እንደ ተናገረው ከሃድያን በምድር ላይ
ያካበቱትን ሥጋዊ ዕውቀት ጥበብ አድርገው ስለሚያስቡ እግዚአብሔርን ይክዱታል፡፡ ይህ ክህደትም ከአንደኛው ትእዛዝ ጋር ይጋጫል፡፡  ሰው በቀጥታ እግዚአብሔር የለም ብሎ ሳይክድ ቃላትን በማሳመር በዕውቀት ብቻ ከብሮ ተግባራዊ ሕይወት ያልተገኘበት ሆኖ እግዚአብሔርን በተግባር የካደው ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡ ቀዳ ቆሮ 119-20 127-31፡፡
እውነተኛ ክርስቲያኖች በዕውቀታቸውና በኃይላቸው የማይመኩ እግዚአብሔርን ከራሳቸው አስቀድመው የሚራመዱ ናቸው፡፡  ስለዚህ በልብ አምነን በአፍ መስክረን እምነታችንን በምግባር ካልገለጥን፣ መልካም ሥራም እየሠራን እግዚአብሔርን እንደ አምላክነቱ ካላመለክን ከሐድያን ከመባል የሚለየን ምንም ነገር ስለማይኖር ከፍርድ አናመልጥም፡፡  ክህደትም እግዚአብሔር የለም ብሎ ተናግሮ መካድ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር የሚወደውን አለማድረግ፣ በኑሮአችን ሁሉ ፈሪሃ እግዚአብሔርን ማጣትነውና ከዚህ መሰል ሕይወት በመራቅ የመጀመሪያውን ሕግ በክህደት የተነሳ ከመጣስ መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡
8. አጋንንትን ማምለክ
እግዚአብሔርን የሚያመልኩት ሕዝብ ሲባሉ አምልኮታቸው ከእግዚአብሔር ውጭ የሆኑ ሁሉ አሕዛብ ይባላሉ፡፡  ልበ አምላክ ዳዊት ‹‹የአሕዛብ አማልክት ሁሉ አጋንንት ናቸውና እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።›› መዝ 955፡፡ በማለት እንደ ተናገረው ጣዖታትን ማምለክ አጋንንትን ማምለክ ነው፡፡  አጋንንትን ማምለክ በጣዖታት ፊት መንበርከክና መስገድ ብቻ ሳይሆን አጋንንትን ማመን፣ በችግር ጊዜ መፍትሔ ከሰይጣን መሻት፣ በክፉ ሥራም ከአጋንንት መተባበር፣ ዕውቀትንና ሀብትን ለማግኘት ሰይጣንን ተስፋ ማድረግ፣ ሰይጣን ያዘዘንን መፈጸምና ይህን የመሰሉ ድርጊቶች ናቸው፡፡
8. አጋንንትን ማምለክ
አንዳንዶች ሰይጣን ስለደረገላቸው ውለታ በመክፈል ሌሎች ደግሞ የሚፈልጉትን እንዲያደርግላቸው ቃል ኪዳን በመግባት ያመልኩታል፡፡ በዚህም የተነሳ ደም በማፍሰስ፣ ጌጦቻቸውን በመስጠት፣ ልጆቻቸውን እንደ መሥዋዕት በማቅረብ ያመልኩታል፡፡  ስለሀብት፣ ስለ ግርማ ሞገሳቸው፣ ስለ ፍቅር፣ ስለሌሎች ፍላጎታቸው በየጠንቋዩ በየቃልቻው ራሳቸውን የሚያባክኑ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ እነዚህም ሁሉ አጋንንትን የሚያመልኩ የአጋንንትንም ፈቃድ የሚያደርጉ ተስፋቸውንም በሰይጣን ላይ ያደረጉ ናቸው፡፡  ሲሞን መሰርይና ለጌቶችዋ በጥንቆላ ብዙ ገንዘብ ታስገባ የነበረችው ገረድ ግኑኝነታቸው ከአጋንንት ጋር ነበር፡፡ ይህም አጋንንት በየዘመኑ ምልክትና ድንቅ በማድረግ የሚያስቱ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ የሐዋ 89 የሐዋ. 1616፡፡ እነዚህም ሰዎች በአጋንንት ኃይል የሚያደርጉት ተአምራት በእግዚአብሔር ኃይል ቅዱሳን ከሚያደርጉት ተአምራት የተለየ ነው፡፡ ቅዱሳን በእግዚአብሔር ስም በመጠቀም በጥላቸው፣ በልብሳቸውፈውሰዋል፡፡  ሰይጣን በቀጥታ እግዚአብሔርን እንድንክደው በማድረግ ወይም የብርሃን መልአክ መስሎ በማታለል ሊቀርበን ይሞክራል፡፡ 2ኛ ቆሮ 1114፡፡
አንዳንድ ሰዎችም በእግዚአብሔር ብቻ ዘንድ የምትታወቀውን የወደፊት ነገራቸውን ለማወቅ ወደ አጋንንት አሠራር ያዘነብላሉ፡፡  ስለዚህ ከላይ በተጠቀሱት የሚያምኑ ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን ክብር ለጣዖታት በመስጠት አንደኛውን ትእዛዝ የተላለፉ ናቸው፡፡  ስለዚህ ክርስቲያኖች ሁላችን ለአጋንንት ተገዢ ከመሆን ራሳችንን ማራቅ ይገባናል፡፡ እግዚአብሔር በሙሴ የነገረንም ይህንኑ ነው፡፡ ‹‹አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ አሕዛብ የሚያደርጉትን ርኵሰት ታደርግ ዘንድ አትማር። ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፥ ምዋርተኛም፥ ሞራ ገላጭም፥ አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ። ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው ስለዚህም
ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል።›› ዘዳግ 189-12፡፡ ‹‹የተቀረፀውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፡፡››  ልናመልከው የሚገባ እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ የተቀረፀውን ምስል ማምለክ የጣዖት አምልኮ እንደሆነ መረዳት ይገባል፡፡  እግዚአብሔርን አምላካችንን ትተን የሰው እጅ ለተጠበባቸው ቅርፃ ቅርፅ መገዛትና ማምለክ አንደኛውን ትእዛዝ መቃረን ነው፡፡  ይህም በእግዚአብሔር ፈቃድ የተሰጡንን ታቦት፣ ጽላት፣ ቅዱሳን ሥዕላትን ማክበርን የሚቃወም አይደለም፡፡ የሰጠን እርሱ ክብር እንድንሰጣቸው ይሻልና፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የምታመልከው የምታስመልከው የአምልኮት ስግደት የሚሰገድለት እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ከእርሱ የተሰጠንንም ሁሉ ደግሞ አክብረን እንይዛለን፡፡  ‹‹የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል፡፡›› ዮሐ 1226 ኢሳ 564-8፡፡ እንደተነገረን በቤተ ክርስቲያን የምናገኛቸው ሥዕሎች የቅዱሳኑን ሕይወት በማፍቀርና በማክበር መልካም ሕይወታቸውን ምሳሌ እንድናደርግ ቅዱስ ጳውሎስም በጽሑፉ ‹‹እንደ ደመና የከበቡን ቅዱሳን ካሉልን…›› ዕብ 121-2፡፡ በማለት የነገረንን በመጠቀም በረከታቸው እንዲደርሰን የምናደርገው ነው፡፡ የተቀረጸውንም ምስል አታድርግ የሚለው ቅዱሳን ሥዕሎችን የተመለከተ አይደለም፡፡ በዘጸ 251-40 እንደተገለጸው ይህን (ታቦት፣ ጽላት፣ ቅዱሳን ሥዕላትን) እግዚአብሔር በፈቃዱ አድርጉ ብሎ ያዘዘን ነውና፡፡ ገላ 31 ሕዝ 41፡፡ እነዚህንም የሚገባውን ክብር ሰጥተን እናከብራቸዋለን እንጂ አናመልካቸውም፡፡
ከላይ እንደተገለጸው ሥዕልም፣ የተቀረፀ ምስልም ቢሆን በእግዚአብሔር ተተክቶ ወይም ተጨማሪ ሆኖ ሊመለክ፣ እንደ አምላክም ፈጽሞ ሊሰገድለት እንደ ማይገባ ቤተ ክርስቲያናችን ታስተምራለች፡፡  ስለዚህ ከላይ የተሰጡንን ትምህርቶች ልብ ብለን በመገንዘብ ከባዕዳን አማልክት አምልኮ መራቅና የመጀመሪያውንም ትእዛዝ መፈጸም ከምዕመናን ሁሉ ይጠበቃል፡፡
ይቆየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

1 comment:

  1. *‹‹ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ይላል።›› መዝ 13፣1
    *በዓለም ላይ ያሉ አምባ ጓሮዎች መነሻቸው ራስን ማምለክ ነው፡፡ ጌታችንም ይህን ከመሰለው እንቅፋት እንድንጠበቅ ‹‹በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ›› ማር 8፣34 ያለን ከዚሁ ራስን የማምለክ ሕይወት እንድንጠበቅ ነው፡፡
    kale hiywet yasemalin

    ReplyDelete