ሰባተኛ ትእዛዝ
‹‹አትስረቅ።›› ዘጸ 20፡15፣
ዘዳግ 5፡19፡፡
‹‹ወይም
ሌቦች
ወይም
ገንዘብን
የሚመኙ
ወይም
ሰካሮች
ወይም
ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት
አይወርሱም።›› ቀዳ ቆሮ 6፡10፡፡
ሌብነት ምንድር ነው? የምንሰርቀውስ
ከማን ነው?
ሌብነት
የአንዱን
ሰው
ንብረት
መካፈል
ማለት
አይደለም፡፡ ‹‹በዚያን
ጊዜ
ኢየሱስ
በሰንበት
ቀን
በእርሻ
መካከል
አለፈ፤
ደቀ መዛሙርቱም ተራቡና እሸት ይቀጥፉ ይበሉም ጀመር። ፈሪሳውያንም አይተው። እነሆ፥ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ማድረግ
ያልተፈቀደውን ያደርጋሉ አሉት።›› ማቴ 12፡1-2፡፡ እንዳለው ደቀ መዛሙርቱን ጌታችን ሲገስጻቸው አልተመለከትንም፡፡ ይህም
የተራበ ሰው በጎዳናው ያገኘው እሸት ቢኖር ከዚያ ቀጥፎ ከረሐቡ እንዲታገስለት ማድርግ የተፈቀደ መሆኑን ያመለክታል፡፡
‹‹ወደ ባልንጀራህ ወይን ቦታ በገባህ ጊዜ እስክትጠግብ ድረስ ከወይኑ ብላ ወደ ዕቃህ ግን ከእርሱ ምንም አታግባ። ወደ ባልንጀራህ እርሻ
በገባህ ጊዜ እሸቱን በእጅህ ቀጥፈህ ብላ ወዳልታጨደው ወደ ባልንጀራህ እህል ግን ማጭድ አታግባ።›› ዘዳግ 23፡24-25፡፡
በባለቤቱ ፈቃድ ተካፍለን ወስደን እንደሆነ ይህ ሌብነት አይባልም፡፡
የተወሰደበት ሰው ሳያውቅ - ይሁዳ
ደቀ
መዛሙርቱ
ሳያውቁ
ለራሱ
እንደወሰደው ወይም ቤቶችን ሰብረው በመግባት ሌቦች
እንደሚያደርጉት ያለ
ድርጊት
ሌብነት
ይባላል፡፡ ‹‹ይህንም
የተናገረ
ሌባ
ስለ
ነበረ
ነው
እንጂ
ለድሆች
ተገድዶላቸው አይደለም፤
ከረጢትም ይዞ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው።›› ዮሐ 12፡6፣ ‹‹ሌቦችም
ቆፍረው
በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ
መዝገብ አትሰብስቡ፡፡›› ማቴ 6፡19፡፡
ነገር ግን ፍጹም ከሆነ በባልንጀርነት የተነሳ ለባልንጀራችን የሆነውን ለራሳችን ብናደርገው እስከነገርነውና ፈቃዱም ሆነ
ይቅርታው እስከተደረገልን ድረስ የምናደርገው ሌብነት አይባልም፡፡ ሌላው
የሌብነት
ዓይነት
ምስጢራዊ
ሌብነት
ነው፡፡
ይህም
ማጭበርበርን ወይም ማታለልን፣ ሕገ ወጥ ሰነድ ማዘጋጀትም ሆነ
መጠቀምን… ይመለከታል፡፡ በዚህ ድርጊት ውስጥ የውሸት ኃጢአት ይገኛል፡፡
ሌብነት ወይም መስረቅ የተሰረቀው ሰው እያየና እየሰማ ያለፈቃዱ ሊፈጸም ይችላል፡፡ ይህም በኃይል ወይም ትጥቅ ታጥቆ
ሊፈጸም ይችላል፡፡ ይህም ድርጊት በተጠቂው ላይ የአካል ጉዳትን ሊያስከትል ይችላል፡፡
መስረቅ ከማውደምም ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡ ሆን ብሎ የሌላውን ሰው ንብረት ማውደምና ንብረቱንም እንዲያጣው ማድረግ
ከሌብነት ሊቆጠር ይችላል፡፡ ይህን ጉዳት ያስከተለ ሰውም ንብረቱን መጠገን ወይም መመለስ ይጠበቅበታል፡፡
ጥላቻውን ለማርካት ብቻ ሆን ብሎ የሌላውን ንብረት የሚያወድም ሰው ፍቅር የጎደለው ሰው ነው፡፡ እንዲህ ያለ ድርጊትም
የሕዝብ
ንብረት
ማውደምን
ይጨምራል፡፡ በጎዳና ግርግር የመንገድ መብራቶችን መሰባበር፣ ዛፎችን መገንደስ፣ የሕዝን
አውቶቡሶችን ማቃጠል የአገርን ሀብትና የሕዝብን ንብረት መስረቅ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
በአጠቃላይ ሌብነት ወይም ስርቆት ለሌሎች ሰዎች መብትና ንብረት ያለንን ንቀት የሚያሳይ ድርጊት ነው፡፡ ሌብነት
የሰራቂውን ሰው ክፋትና አለመታመን የሚያሳይ፣ በሰውም ዘንድ ያለውን ተቀባይነት የሚያሳጣ ሰውም እንዳይቀርበው
የሚያደርግ ድርጊት ነው፡፡ ይሁን
እንጂ
ይህ
ጉዳይ
የራሳቸውንና የሌላውን ሰው ቁሳቁስና ንብረት ለይተው ለመረዳት በማይቻላቸው ለጋ ወጣቶች ቢከሰት
ፈጽመን እንዳናገላቸው መጠንቀቅ ያስፈልገናል፡፡ በእውቀት፣ ሥነልቦናና ስሜት እየበሰሉ ሲሄዱ ራሳቸው ይስተካከላሉና፡፡ ሌብነት
አንዳንድ
ጊዜ
ቅጣትን
ሳይሆን
ሥነ-ልቦናዊ ሕክምናን የሚፈልግ ሕመም ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ሕመም ያለበት ሰው
እንዴት እንደሚጠቀምበት የማያውቀውን ማንኛውንም ያገኘውን ቁሳቁስ ወስዶ ሊያስቀምጥ ወይም ከሌሎች እይታ ሊሰውረው
ይችላል፡፡ የሚያደርገውም ከቁጥጥሩ ውጪ በሆነ መንገድ ስለሆነ ባደረገውም ፈጽሞ ሊያለቅስ ይችላል፡፡ እንዲህ ያለው ሰው
ችግር ከቀድሞ ታሪኩ፣ ከኖረበት ወይም ካደገበት አካባቢ ተጽእኖ፣ ከአስተዳደጉ የመነጨ ሊሆን ይችላል፡፡
እርስ በርስ በመተማመን በእርጋታ መኖር ምን ያህል የሚያስደስት ነው? ማንኛውንም ነገር በየትኛውም ሥፍራ አስቀምጠን
ተመልሰን ማንም ሳይነካው ማግኘት፣ በራችንን ከፍተን ሄደን ተመልሰን ያለምንም ችግር መልሰን ማግኘት ምንኛ መልካም ነው!
ላባም ያዕቆብን ‹‹ ነገር
ግን
አምላኮቼን (ጣዖታቱን) ለምን ሰረቅህ?›› ዘፍጥ 31፡30፡፡ ብሎ በወነጀለው ጊዜ ያዕቆብ የጥፋቱን ክብደት
ተረድቶ ‹‹
አምላኮችህን የምታገኝበት ሰው ግን እርሱ ይሙት የአንተ የሆነውም በእኔ ዘንድ ይገኝ እንደ ሆነ በወንድሞቻችን ፊት ፈልግ፥
ለአንተም ውሰደው አለ። ›› ያዕ
31፡32፡፡ ይህም የተከሰተው ቅዱሱ ትእዛዝ ከመሰጠቱ በፊት ነበር፡፡
ይህን የሚመስለውም ቅጣት በዮሴፍና በወንድሞቹ ታሪክ ውስጥ ይገኛል፡፡ ወንድሞቹ ጽዋውን ሰርቃችኋል ተብለው በተከሰሱ ጊዜ
‹‹ ጌታዬ እንደዚህ ያለውን ቃል ለምን ይናገራል? ባሪያዎችህ ይህን ነገር የሚያደርጉ አይደሉም። እነሆ፥ በዓይበታችን አፍ ያገኘነውን ብር
ይዘን ከከነዓን አገር ወደ አንተ ተመልሰናል ከጌታህ ቤት ወርቅ ወይስ ብር እንዴት እንሰርቃለን? ከባሪያዎችህ ጽዋው የተገኘበት እርሱ
ይሙት እኛም ደግሞ ለጌታችን ባሪያዎች እንሁን።›› ዘፍጥ 44፡7-9፡፡ ብለዋል፡፡
የማይዋሽ ሌባ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ሌባ የሆነ ሁሉ የሠራውን ጥፋት ለመሸፈን ይዋሻል፡፡ ሌባ ከሰረቀ በኋላ ብቻ ሳይሆን
የሚሰርቀውን ሰው ለማታለል ሲል ሳይሰርቅም በፊት ይዋሻል፡፡ ስለዚህ ስለመስረቃችን በምንናዘዝበት ጊዜ ስለመዋሸታችንም
መናዘዛችንን አንርሳ፡፡
የምንሰርቀው ከማን ወይም ምን ነው?
1. ከድሆች
ከድሆች፣ ወላጅ አልባ ከሆኑ ልጆች፣ ባልዋ ከሞተባት ሴት መስረቅ በሌባው ልብ ምንም መልካምነት እንደሌለ ስለሚያመለክት ታላቅ
ኃጢአት ነው፡፡ ጌታችንም ‹‹ እናንተ
ግብዞች
ጻፎችና
ፈሪሳውያን፥ በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥
ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ።›› ማቴ 23፡14፣ ‹‹ የመበለቶችን ቤት የሚበሉ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ
እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ። ›› ማር
12፡40፡፡ በማለት ጻፎችና ፈሪሳውያንን የወቀሰው ለዚሁ ነው፡፡ እንዲህ ያሉትን በፍቅር መርዳት
ሲገባን ለዳቦ መቅመሻ ያገኙአትን መንጠቅ ጭካኔ ነው፡፡ ‹‹ ከአንተ ጋር ለተቀመጠው ለወገኔ ለድሀው ገንዘብ ብታበድረው፥ እንደ ባለ አራጣ አትሁን፥ አራጣም አትጫንበት። የባልንጀራህን
ልብስ ለመያዣ ብትወስድ ፀሐይ ሳትገባ መልስለት፤ ሥጋውን የሚከድንበት እርሱ ብቻ ነውና የሚተኛበትም ሌላ የለውምና ወደ እኔም
ቢጮኽ መሐሪ ነኝና እሰማዋለሁ።›› ዘጸ 22፡25-27፡፡
‹‹
ወንድምህ
ቢደኸይ
እጁም
በአንተ
ዘንድ
ቢደክም፥
አጽናው
እንደ
እንግዳና
እንደ
መጻተኛም
ከአንተ
ጋር
ይኑር።
ወንድምህ
ከአንተ
ጋር ይኖር ዘንድ ከእርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አትውሰድ ነገር ግን አምላክህን ፍራ። ብርህን በወለድ አታበድረው መኖህንም በትርፍ
አትስጠው።›› ዘሌዋ 25፡35-37፡፡ ‹‹ ለወንድምህ በወለድ አታበድር የብር ወይም የእህል ወይም የማናቸውንም ነገር ሁሉ ወለድ አትውሰድ።›› ዘዳግ 23፡19፡፡ ኣራጣ
አበዳሪ
ከድሃው
የሚወስደው የበዛ ገንዘብ የድሃውን መሠረታዊ ነገር እንደመንጠቅ ወይም እንደ መስረቅ ይቆጥራል፡፡
ባለጠጋውን መስረቅ ኃጢአት ከሆነ እንግዲህ ድሃውንም መስረቅ የባሰ ኃጢአት ነው፡፡
2.
ከተራ ሰዎች መስረቅ ኃጢአት ከሆነ ቤተ ክርስቲያንን ወይም
ካህናትን መስረቅስ እንዴት ይታያል?
ንዋየ ቅዱሳትን ወይም አብያተ ክርስቲያናትን መስረቅ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው፡፡ በመላው ዓለም የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት
ከያዙአቸው ቅርሶች ጋር ያለጠባቂ ክፍት ሆነው ሳይዘጉ የምናገኛቸው ለዚሁ ነው፡፡
ወደ እግዚአብሔር ቤት የምንመጣው ለንስሐ ነው፡፡ ሻማ፣ መጻሕፍትን፣ ጫማ…የሚሰርቁ ምን ይባላሉ? ከቤተ
ክርስቲያን አልባሳት፣ ገንዘብ፣ … ለራሳቸው
ወይም
ለቤታቸው
የሚሰርቁስ? ይህ የእግዚአብሔር፣ የድሆችና የተቀደሰ ገንዘብ ነው፡፡ የቅዱሳንን አጽም፣ ታሪካዊ ቅርሶችን…የሚሰርቁስ? የላሊበላ መስቀል (ተመልሷል)፣ በርካታ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት፣
ጽላቶች/ታቦታት፣ …ከገዳማት
ከአብያተ
ክርስቲያናት ‹‹ለእውቀት
ባለን
ጥማት…›› ያደረግነው ነው በሚል ሰበብ ተሰርቀዋል፡፡ ከሁሉ
በላይ
ደግሞ
እግዚአብሔርን ራሱ የሚሰርቁትንስ ምን እንላቸዋለን? አሥራቱን፣ በኩራቱንና ቀዳምያቱን ከመስጠት ተከልክለው
እግዚአብሔርን የሚሰርቁት አሉ፡፡ ይህም ጉዳይ ‹‹ ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምር ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም
አልጠበቃችሁም። ወደ
እኔ
ተመለሱ፥
እኔም
ወደ
እናንተ
እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦ እናንተ ግን፦ የምንመለሰው
በምንድር
ነው? ብላችኋል። ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ። በቤቴ ውስጥ
መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ
ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡›› ሚል 3፡7-10፡፡ ይህ
ገንዘብ
የቤተ
ክርስቲያንና የድሆች ገንዘብ ነው፡፡ ለባለቤቱ ባለመስጠታችንም የተነሳ ጌታችን ‹‹ የዓመፃ
ገንዘብ
ሲያልቅ
በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ።›› ሉቃ 16፡9፡፡ በማለት ነግሮናል፡፡
3. ሌላው ከእግዚአብሔር ና ከቤተ ክርስቲያን የምንሰርቀው ጊዜን ነው፡፡ የሰረቅነውንም ለራሳችን
እንጠቀምበታለን፡፡ ለምሳሌም
1. የጌታን ቀን (ሰንበት)
፡- እግዚአብሔር በሳምንት ለእርሱ የምናደርጋት ዕለት (ሰንበት) አለችው፡፡ በዚያች ዕለት ለራሳችን እንደፈለግን
እንድናደርግ አይገባንም፤ ዕለቲቱ ለእግዚአብሔርና ለአምልኮቱ ናትና፡፡ ለራሳችን የሥጋ ጉዳይ ካዋልን ግን የእግዚአብሔርን ቀን
ሰርቀነዋል ማለት ነው፡፡
2. የአምልኮ ጊዜያት፡- በየዕለቱ ለጸሎት፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማንበብ፣ ለቅዳሴ (ለኪዳን) … መንፈሳዊ ጉባኤያትን ለመሳተፍ
ለእግዚአብሔር የሆነ ጊዜ አለ፡፡ እነዚህን ለማድረግ ዕድደ የማንሰጥ ከሆንን ከእግዚአብሔር እየሰረቅን ነው ማለት ነው፡፡ ‹‹ አምላኬ፥አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።›› መዝ
62(63)፡1፣
‹‹ እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥ ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል።›› ምሳ 8፡17፡፡ ያለን ለዚሁ ነው፡፡ እያንዳንዱን ዕለት
ያለእግዚአብሔር የምንጀምር ከሆንን እግዚአብሔርን እየሰረቅን ነው ማለት ነው፡፡
3. የእግዚአብሔር በዓላት፡- እግዚአብሔር ለርሱ ብቻ የምናደርጋቸው የበዓላት ዕለታት አሉት፡፡ ለምሳሌ ሰሙነ ሕማማት፣ ትንሳኤ፣ ልደት፣
ስቅለት
…ለእግዚአብሔር ካላደረግናቸው ሰርቀነዋል ማለት ነው፡፡ ባሎች/ሚስቶች የወር ገቢያቸውን ባይገልጹ ወይም ቀንሰው ባያሳውቁ ሌብነት ነው፡፡ ማንኛውም ለባል የሆነ የሚስት እንደሆነ በግልጽ
ተጋቢዎች የሆኑ ክርስቲያኖች ሁሉ መረዳት ይገባቸዋል፡፡ የመሥሪያ
ቤታችንን
ቁሳቁስ፣
መኪና፣
አለቆች
ከሆንን
የበታች
ሠራተኞቻችንን ጉልበት ሳይቀር ለግላችን ወይም ለራሳችን መጠቀም ቀላል
ቢመስልም ስርቆት ነው፡፡ የተዋስነውን ነገር ሳይፈቀድልን አረሳስተን ማስቀረትም ሌብነት ነው፡፡ ብዙዎች በዚህ መንገድ እስክሪብቶ፣ መጻሕፍቶቻቸውን አጥተዋል፡፡
ስለዚህ ስንዋስ ከማን እንደተዋስነው የሚገልጽ ማስታወሻ ከእቃው ጋር አብረን ብናስቀምጥ ለመመለስ ይረዳናል፡፡
4. በንግድ ዘርፍ የሚፈጸም ስርቆት
1. በማታለል መስረቅ፡- የተበላሸ ዕቃን ገዢው አለማስተዋሉን ምክንያት አድርገን መሸጥ፡፡ ገዢው ትኩረቱን ወደ ብልሽቱ እንዲያደርግ ማድረግ
ብንችል ምንኛ ውብ ነው፡፡ በአትልክትና ፍራፍሬ መካከል የተበላሸውን፣ በከሰሉ ሥር የደቀቀውን፣… መሸጥ ስርቆት ነው፡፡ የንግድ ምልክቶችን
በመውሰድ አስመስሎ ሠርቶ/አምርቶ (ብረቱን
ወርቅማ
ቀለም
ቀብቶ
አስመስሎ) ጥራቱን ያልጠበቀ ነገር መሸጥ ራሱ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ
የሸማቾችን ገንዘብ መንጠቅ ዌወም መስረቅ ነው፡፡ እንዲህ ባለ ሥራ የተጠመዱትም በሐሰት ፕሮፖጋንዳቸው የበዛ የማታለል ሥራ መሥራታቸው
ኃጢአቱን የከፋ ያደርገዋል፡፡ የመለኪያ ሚዛኖችን ተጠቅሞም ማታለል ከዚሁ ይመደባል፡፡ ተጠቃሚውም በዚህ ድርጊት የተነሳ መጠንን በማሳነስ
ማታለል ይፈጸምበታል፡፡
2. በስግብግብነትና ዋጋን በመጨመር መስረቅ፡- እግዚአብሔር ተገቢ የሆነ ትርፍ ከማግኘት በቀር ከራስ ወዳድነት የተነሳ ትርፍ እንድናግበሰብስ
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ
ሃይማኖታችን አልፈቀደልንም፡፡ ይህም ያልተፈቀደ ድርጊት በሞኖፖል (ምርትን) ለብቻ በመያዝ ገዢውን በማስጨነቅ
ይፈጸማል፡፡ ምርቱን ሁሉ ከገበያ አሟጦ በመግዛት ከገበያ በማጥፋት በራስ ተመን ገዢውን ማስጨነቅ፡፡
3. ኢኮኖሚያዊ ስርቆት፡- ዋጋን ከፍና ዝቅ በማድረግ ዝቅተኛ አቅም ያላቸውን ነጋዴዎች ከገበያ በማውጣት የሚፈጸም ስርቆትም ከዚሁ ይመደባል፡፡
4. በሸማቾች የሚፈጸም ስርቆት፡- ሸማቾች በሚያደርጉት ክርክር ሻጩ የማስረዳት አቅም ከማጣት የተነሳ ወይም ሌሎች ክፍተቶችን በመጠቀም
ራሳቸውንና ቤተ ሰቦቻቸውን ለመመገብ የማይበቃ ትርፍ እያተረፉ እንዲሸጡ ማታለል ስርቆት ነው፡፡
5 ኢፍትሐዊነትና የሠራተኞችን ደመወዝ አለመክፈል
1. ለሠራተኞች ተመጣጣኝ የሆነ ደመወዝ አለመክፈል መስረቅ ብቻ ሳይሆን መግደልም ነው፡፡ ‹‹ እግዚአብሔርም አለ፦ በግብፅ
ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ፡፡›› ዘጸ 3፡7፣ ‹‹ እነሆ፥
እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፥ የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ፀባዖት
ጆሮ ገብቶአል።›› ያዕ 5፡4፡፡
2. ደመወዝ ማዘግየትን ወይም ዕድገትን መከልከልን ስርቆት መሆኑን አስመልክቶም ‹‹ድሀና
ችግረኛ
የሆነውን
ምንደኛ፥ ከወንድሞችህ ወይም በምድርህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ከሚቀመጡት መጻተኞች ቢሆን፥ አታስጨንቀው። ድሀ ነውና፥ ነፍሱም
ጠንክራ ትፈልገዋለችና ወደ እግዚአብሔር እንዳይጮኽብህ ኃጢአትም እንዳይሆንብህ ደመወዙን ፀሐይ ሳይገባ በቀኑ ስጠው።›› ዘዳግ 24፡14-15፡፡ ብሎናል፡፡ ይህም መክፍል ከሚገባቸው በላይ ወይም በታች የሚገምቱ የግብር ሰብሳቢ አካል ሠራተኞችንም
ይመለከታል፡፡ ሉቃ 19፡8፡፡
3. ጉቦ፡- ለሠራው ሥራ ደመወዙን የሚቀበል ሠራተኛ አገልግሎት ከሰጠው ወገን ሌላ ምንም መጠበቅ የለበትም፡፡ ጉቦ የሚቀበል
ከሆነ ግን ስርቆት ነው፡፡ ጉቦን መቀበልም በመንግሥት የተጫነበትን ግብር ለማስቀነስ፣ ጉዳዩን ከተገቢው ጊዜ በላይ ለማፋጠን
… ሲባል ነው፡፡ አገልግሎት ካገኘንበት ምግብ ቤት የሚገኙ ገቢያቸው አነስተኛ ለሆኑ ሠራተኞች የምንሰጠው ቲፕ ግን ጉቦ
አይባልም፡፡
4. በሥራ ገበታ ላይ አለመታመን፡- ተገቢ
ያልሆነ
ፈቃድ
በመውሰድ
ወይም
የሥራ
ሰዓት
ባለማክበር፣ ታምኖ በተገቢው ፍጥነትና
ብቃት ሥራን አለመሥራት፣ ለሥራ የምንገለገልባቸውን ቁሳቁሶች ያላግባብ ማውደም ስርቆት ነው፡፡ ለዚህ ጉዳይ የራሳቸውን
ታክሲ የሚያሽከረክሩና ተቀጥረው የሚያሽከረክሩ ሾፌሮች ጥሩ ማሳያ ምሳሌዎች ናቸው፡፡
5. ሥልጣንን በመጠቀም ሕገ ወጥ ስምምነቶችን (ኮንትራት
ውሎችን
መፈጸም) ማድረግ ወይም የሌላውን ንብረት መውሰድ ቀዳ
ነገ 20፡1-ፍም፣ ሕግን ለራስ አመቺ በሆነ መንገድ እያጣመሙ በመተርጎምም ራስን ተጠቃሚ ማድረግ ስርቆት ነው፡፡
6. ስምምነትን ወይም ውልን በማፍረስ መስረቅ
1. ውልን ማፍረስ ‹‹ማናቸውም
ሰው
ኃጢአትን
ቢሠራ፥
እግዚአብሔርንም ቢበድል፥ ያኖረበትን አደራ ወይም ብድር ወስዶ
ባልንጀራውን ቢክድ፥ ወይም ቢቀማ፥ ወይም በባልንጀራው ላይ ግፍ ቢያደርግ ወይም የጠፋውን ነገር ቢያገኝ፥ ያንንም ሸሽጎ
በሐሰት ቢምል፥ ሰው ከሚያደርጋቸው ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በአንዲቱ ቢበድል፥ እርሱ ኃጢአትን ሠርቶ በደለኛ ቢሆን፥ በቅሚያ
የወሰደውን ወይም በግፍ የተቀበለውን ወይም የተሰጠውን አደራ ወይም ጠፍቶ ያገኘውን፥ ወይም በሐሰት የማለበትን ነገር
ይመልስ በሙሉ ይመልስ፥ ከዚያም በላይ አምስተኛውን ክፍል ጨምሮ የበደሉን መሥዋዕት በሚያቀርብበት ቀን ለባለ ገንዘቡ
ይስጠው። ስለ በደል መሥዋዕትም ለእግዚአብሔር ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ እንደ ግምጋሜህ መጠን ስለ በደል
መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያምጣ።ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል፥ ስለዚያም ስላደረገው በደል ሁሉ ይቅር ይባላል። ›› ዘሌዋ
6፡2-7፡፡ በማለት ንስሐ የሚያሻው ኃጢአት መሆኑን ይነግረናል፡፡
2. በገንዘብ ልውውጥ ጊዜ በስህተት አልፎ የተሰጠንን ገንዘብ በሙሉ አለመመለስም ስርቆት ነው፡፡
3. በቁማር ከሌላው ሰው የተወሰደ ገንዘብም ያለፍትሕ የተወሰደ ስለሆነ ስርቆት ነው፡፡ ሕጻናትን አታሎ ገንዘባቸውን መውሰድም
እንዲሁ
ስርቆት
ነው፡፡
4. በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ በሌብነት ድርጊት ተባባሪ መሆን ራሱ ሌብነት ሆኖ ይቆጠራል፡፡ ‹‹ ከሌባ
ጋር
የሚካፈል
ነፍሱን
ይጠላል
መርገምን
ይሰማል፡፡›› ምሳ 29፡24፡፡
7. የሰውን በጎ ሐሳብ ወይም ምስጢር መስረቅ
1. የአንድን ሰው ጽሑፍ፣ ግጥም፣ ዜማ፣ እቅድ ወይም በአጠቃላይ ሥራ ወስዶ የራስ አስመስሎ ማቅረብ ስርቆት ነው፡፡
2. በፈተና ወቅት መስረቅ፣ የአንድ ሰው ፈጠራ፣ የትምህርት መረጃ፣ ሐሳቡን መስረቅ ወይም በማንኛውም የሥልጣን እርከን ለጉዳዩ ተባባሪ
መሆን
ስርቆት
ነው፡፡
3. ምስጢርን መስረቅ፡- የሰውን ደብዳቤ ማንበብ (የልጆቻችንንም ቢሆን አሳምነን ወይም በንስሐ አባቶቻችን ፈቃድ እንዲያምኑበት
አድርገን ክላሆነ በቀር)
፣ መስማት የሌለብንን መስማት፣ … ሌብነት
ነው፡፡
8. ሌሎች የስርቆት ዓይነቶች
አገርን በቅኝ ገዢነት ወይም በኃይል በመውረር ፣ ነፍሳትን በክህደት ትምህርት ወይም እንግዳ ትምህርትን በሚከተሉ አማካይነት መስረቅ
ሌብነት ነው፡፡ ዮሐ 10፡8፡፡ ታላቁ የሕግ መምህር ገማልያል ‹‹ ከዚህ
ወራት
አስቀድሞ
ቴዎዳስ።
እኔ
ታላቅ
ነኝ
ብሎ
ተነሥቶ
ነበርና፥
አራት
መቶ
የሚያህሉ
ሰዎችም
ከእርሱ
ጋር
ተባበሩ፤
እርሱም
ጠፋ
የሰሙትም
ሁሉ
ተበተኑ
እንደ
ምናምንም
ሆኑ።
ከዚህ
በኋላ
ሰዎች
በተጻፉበት ዘመን
የገሊላው
ይሁዳ
ተነሣ
ብዙ
ሰዎችንም
አሸፍቶ
አስከተለ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበታተኑ። አሁንም እላችኋለሁ። ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ
ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥
በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።›› የሐዋ 5፡36-39፡፡ በማለት ስለዚሁ ሰራቂዎችንና እውነተኞቹን በማንሳት
አውስቷል፡፡ እነዚህም የአርዮስ፣ የመቅዶንዮስ፣ የንስጥሮስ…ተከታዮች ሆነው የበተ ክርስቲያንን ልጆች የሚነጥቁ ናቸው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍም እነዚህኑ
አስመልክቶ ‹‹
ማንም
ወደ
እናንተ
ቢመጣ
ይህንም
ትምህርት
ባያመጣ
በቤታችሁ
አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ
ሥራው ይካፈላልና።›› ካል ዮሐ 10-11፡፡
በማለት
ያስጠነቅቀናል፡፡ ለስርቆት የሚያነሳሱ ምክንያቶች
ክፉ ምኞት፣ ገንዘብን መውደድ፣ ለሌሎች ፍቅር ማጣት፣ የሌሎችን መብት አለማክበር፣ ጭካኔ፣ ምሕረት የለሽ መሆን.. ሊጠቀሱ የሚችሉ ለስርቆት የሚያነሳሱ ምክንያቶች ናቸው፡፡
ከቤተሰብ ሌብነትን መውረስ፣ አስመሳይነት ወይም የተበላሸ አስተዳደግና፣ ድህነትም ለሌብነት መነሻ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሌብነት
ለደከመች
ነፍስ
በሽታ፣
ልምድ
ወይም
ደስታ
ሊሆን
ይችላል፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ‹‹ የስርቆት
ውኃ
ይጣፍጣል፥ የተሸሸገም እንጀራ ደስ ያሰኛል።›› ምሳ 9፡17፡፡ በማለት
እንደጻፈልን፡፡ ሌብነት በባለጠጎች ሲፈጸም ስግግብነት ወይም በሽታና ገንዘብን መውደድ ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ‹‹ ፈሳሾች
ሁሉ
ወደ
ባሕር
ይሄዳሉ፥
ባሕሩ
ግን
አይሞላም
ፈሳሾች
ወደሚሄዱበት ስፍራ እንደ ገና ወደዚያ ይመለሳሉ።›› መክ 1፡7፡፡ በማለት እንደጻፈልን፡፡ በድሆች
የተፈጸመ
ስርቆትም
ጉድለታቸውን ለመሙላት ያደረጉት ስለሆነ ፍትሐዊ ሆኖ አይቆጠርም፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ‹‹ ሌባ
በተራበ
ጊዜ
ነፍሱን
ሊያጠግብ
ቢሰርቅ
ሰዎች አይንቁትም ቢያዝም ሰባት እጥፍ ይከፍላል፥ በቤቱም ያለውን ሁሉ ይሰጣል።›› ምሳ 6፡30-31፡፡ በማለት እንደጻፈልን፡፡
መፍትሔዎች የመጀመሪያው መፍትሔ
የታማኝነትን፣ ሌሎችን የምንወድበትን ጽኑ ፍቅርና መብታቸውን የምናከብርበትን ይዘን ሕይወት ይዘን ከልጅነት ዘምሮ አብሮ ማደግ ነው፡፡
እንደዚህ ካደግን ጠፍቶ ተተገኘነውን ለባለቤቱ የመመለስ፣ እርስ በርስም የመከባከብ ሕይወት ይኖረናል፡፡
ሌላች መፍትሔዎች ጠንክሮ መሥራት፣ ያለኝ ይበቃኛል ማለት፣ ቅንጦትን አለመውደድ፣ እንደ አቅም መኖር፣ በየጭፈራ ቤቱ አለመገኘት፣ ከትዳር ውጪ ግኑኝነትን
አለመመሥረት፣ ቅማርተኝነትን ከራስ ማራቅ፣ ወዘተ ናቸው፡፡
ለስርቆት የሚያስፈልግ ንስሐ መናዘዝና
የወሰዱትን መመለስ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ‹‹ እርሱ
ኃጢአትን
ሠርቶ
በደለኛ
ቢሆን፥
በቅሚያ
የወሰደውን ወይም በግፍ የተቀበለውን ወይም የተሰጠውን
አደራ ወይም ጠፍቶ ያገኘውን፥ ወይም በሐሰት የማለበትን ነገር ይመልስ በሙሉ ይመልስ፥ ከዚያም በላይ አምስተኛውን ክፍል ጨምሮ የበደሉን መሥዋዕት
በሚያቀርብበት ቀን ለባለ ገንዘቡ ይስጠው።…›› ዘሌዋ 6፡4-5፡፡፣ ‹‹ ሰው
በሬ
ወይም
በግ
ቢሰርቅ፥
ቢያርደው
ወይም
ቢሸጠው፥
በበሬው
ፋንታ
አምስት
በሬዎች፥ በበጉም ፋንታ አራት በጎች ይክፈል።›› ዘጸ 22፡1፣ ዘጸ 227-8፣
ምሳ
6፡30-31፡፡
ዘኬዎስ ‹‹ ጌታ
ሆይ፥
ካለኝ
ሁሉ
እኵሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደ ሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው።›› ሉቃ 19፡8፡፡ እንደተናገረውሌባ የሰረቀውን እጥፍ አድርጎ ቢያንስ የሰረቀውን መመለስ ይኖርበታል፡፡ ይህን ሲያደርግ ማንነቱ እንዲገለጥ ካልፈለገ ደግሞ መመለስ የሚያስችለውን ሌላ ጤናማ
መንገድ ማዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
ምንጭ:
-ሕግጋተ እግዚአብሔር ብፁዕ
ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ 3ኛ
/ ትርጉም ቀሲስ እሸቱ ታደሰ/
ማኅበረ ቅዱሳን 1995 ዓ.ም

No comments:
Post a Comment