Thursday, August 16, 2012

ደብረ ታቦር




በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን


ደብረ ታቦር E ቋንቋ ሲሆን የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ማቴ 71-8 የታቦር ተራራ የሚገኘው ሁን ፍልስጥኤም ተብሎ በሚጠራው ሀገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም የታቦር ተራራ ጌታችን ምላካችን የሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ XEንደ ፀሐይ የበራበት ልብሱም ንደ ብርሃን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ከሚከበሩት ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት ንዱ ደብረ ታቦር ነው፡፡ በዓሉ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን በድምቀት ይከበራል፡፡ ታቦር ከገሊላ ባሕር በምራባዊ ደቡብ በኩል 10. ርቆ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ይህ ተራራ ከባሕር ጠለል 572 ሜትር ከፍታ ለው፡፡ «ባርቅ የተባለው ጦረኛ ሕዝበ Eስራኤልን ይዞ በመዝመት ሲራ የተባለውን የሕዝብ ጠላት በታቦር ድል ነስቶ ሸንፏል” መሳፍንት 46­-14፡፡

ልበ xምላክ ቅዱስ ዳዊትም ታቦርና xርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል፡፡ ክንድህ ከኃይል ጋር ነው ሲል በመዝሙር 8812 ስለ ታቦር ተራራ ዘምሯል፡፡ የታቦር ተራራ በገሊላ ከሚገኙ ተራራዎች ንደኛው ሲሆን በዛብሎን ክፍል ውስጥ ለሚኖሩ ልጆች የተሰጠ ቦታ ነው፡፡ 1 ዜና.677 ሐዲስ ኪዳን ግን ረጅም ተራራ ከማለት በስተቀር ታቦር ብሎ ስሙን ይጠራውም፡፡ ሆኖም ክርስቶስ በዚህ ተራራ ላይ ክብሩን ንደገለጠና የዚህም ተራራ ስም ታቦር መሆኑን ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው ገልጠዋል፡፡ ትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም ይህንን ረጅም ተራራ ደብረ ታቦር Eያለ በድጓው ስፍቶ ጽፏል፡፡  ጌታችን የሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ረጅም ተራራ የወጣው ብርሃነ መለኮቱን ክብሩን ለመግለጽ ነው፡፡ በዚህ ተራራ ጌታችን የሱስ ክርስቶስ ከሙሴና ከኤልያስ ጋር ተነጋግሮል፡፡ነዚህም ሁለት ታላላቅ ሰዎች በበብሉይ ኪዳን ጊዜ ስለ ክርስቶስ ትንቢት የተናገሩ ስለ ግዚብሔር መንግሥት ያስተማሩ ቅዱሳን ነቢያት ነበሩ፡፡ ከነቢያት መካከል ሁለቱ ቅዱሳን ነቢያት Eንዲገኙ ያደረገውም ጌታችን የሱስ ክርስቶስ በቂሣርያ ተገኝቶ «ደቀ መዛሙርቱን ሰዎች ኔን ማን ይሉኛል) ሲል ጠየቃቸው Eነሱም ንዳንዶቹ ኤልያስ፣ ንዳንዶቹም ሙሴ፣ ነው ይሉሃል ሉት፡፡Eናንተስ ማን ትሉኛላችሁ) ቢላቸው ብዛኛዎቹ ኅብረተሰቡ ከሚለው ጋር ሲተባበሩ ቅዱስ ጴጥሮስ ግን ንተ ክርስቶስ የሕያው ግዚብሔር ልጅ ነህ ሲል መሰከረ፤የሱስም መልሶ ይህን በሰማያት ያለው ባቴ Eንጂ ሥጋና ደም ልገለጠልህምና ብፁዕE ነህ ለው፡፡ማቴ.1613-18፡፡ በዚህ ኳኋን ወደ ደብረ ታቦር ተራራ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን ይዞ ወጥቶ ራሱ ኤልያስ ወይም ሙሴ ለመሆኑን ገለጠላቸው፡፡ ከሞተ ብዙ ዘመን የሆነውን ሙሴን ከመቃብር ስነስቶ ቀጥሎም Eሳት ሠረገላ ያረገውንና በተድላ ገነት የሚኖረውን ኤልያስን በተራራው Eንዲገኝ ድርጐ ብረውት የነበሩት ደቀ መዛሙርት ሙሴ ነው ወይም ኤልያስ ነው በማለት ሲጠራጠሩ Eንዳይኖሩ ትምህርት ለመስጠት ነው፡፡
ማቴ.172 «በፊታቸው ተለወጠ ፊቱም ንደ ፀሐይ በራ ልብሱም Eንደ ብርሃን ነጭ ሆነ ይላል፡፡ ክርስቶስ ፊቱ Eንደ ፀሐይ የበራው የብርሃኑም ኃይል ያንፀባረቀው የብሉይ ኪዳን መሪ ንደነበረው ንደ ሙሴ ፊት ብርሃን ይደለም፡፡ «ሙሴ ከሲና ተራራ ሲወርድ የፊቱ ቆዳ ንፀባረቀ ሮንና Eስራኤልም ይህንን ስላዩ ወደ ይቀርቡ ዘንድ ፈሩ ተሸፈንም ያሉ ጮኹ «ሙሴም ግዚብሔር ያዘዘውን Eነሱ ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ በፊቱ መሸፈኛ ደረገ ይላል፡፡  ዘፀ. 3429-30፡፡ የሙሴ የጸጋ ነው ክርስቶስ ግን የባሕርይ ነው፡፡ «ብሩህ ደመና ጋረዳቸው” ይላል ይህ በሲና ንደታየው ያለ ይደለም፡፡ በታቦር የታየው ግን ብሩህ ነበር፡፡ በደብረ ሲና የተገለጠ የፍጡር የሙሴ ክብር ነበር፤ በደብረ ታቦር ግን የሕያው ባሕርይ ክርስቶስ ክብር ተገልጦል፡፡

የደብረ ታቦር በዓል በቤተ ክርስቲያን በኩል ያለው ከባበር፡-

1. ደብረ ታቦር ከዘጠኙ Aበይት በዓላተ ግዚ ንዱ ነው

ከዋዜማው ጀምሮ ስከ በዓሉ ፍጻሜ ድረስ ማኅሌት ይቆማል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ስለ በዓሉ የደረሰው መዝሙር ይዘመራል፡፡ «ሰበሕኩከ በደብር በቅድመ ሙሴ ወኤልያስ ነቢያት Eምዕመናኒከ በታማኞችህ ነቢያት በሙሴና በኤልያስ ፊት የባሕርይ ልጅነትህን መሰከርሁልህ የሚለው መዝሙር ለበዐሉ ልዩ ድምቀት ስጥቶት ይውላል፡፡

2. የደብረ ታቦር በዓል በቆሎ ተማሪዎች በኩል ያለው ይዞታ

የቆሎ ተማሪዎች በዓሉ ንድ ወር ሲቀረው በየመንደሩ ተዘዋውረው ጥሬ በልመና ይሰበስባሉ፤ ከለመኑትም ጥሬ ግማሹን ጠላ ይጠምቃሉ፣ ግማሹን ቆሎ ይቆሉታል፡፡ በዚህ ሁኔታ ሲዘጋጁ ይሰነብቱና በደብረ ታቦር ለት የለመኑትን ኅብረተሰብ የደብሩን ካህናትና ለቃ ስተማሪዎቻቸውን ጠርተው ይጋብዛሉ፡፡ በሚጋብዙበትም ወቅት Eየዘመሩ ተጋባዡን ያስደስቱታል፡፡

3. የደብረ ታቦር በዓል ከኅብረተሰቡ ጋር ያለው የባህል ግንኙነት

ማንኛውም ኅብረተሰብ በዋዜማውና በዕለቱ ችቦ ያበራ ያከብረዋል፡፡ ሴቶችም በዋዜማው ንደ ጥብኝ ወይም ሙልሙል ድርገው ከስንዴ ዱቄት የተቦካ ዳቦ በብዛት ይጋግራሉ ወደ ቤት ሊጠይቅ ለሚመጣ ሰው ሁሉ ዳቦ ያቀርቡለታል፡፡ በጠቅላላው ዘመድ ዝማዱ ዳቦ የተያዘ የሚጠያየቅበት የተነፋፈቀ ሁሉ የሚገናኝበት የተራራቀ ሁሉ የሚቀራረብበት በዓል በመሆኑ በዓሉ በኅብረተሰቡ ዘንድ ከፍ ያለ ተወዳጅነት ለው፡፡

4. የደብረ ታቦር በዓል በልጆች በኩል ያለው ሁኔታ

ወንዶች ልጆች ከዋዜማው ጀምሮ በቡድን፣ በቡድንዘ እየተከፋፈሉ ዳቦና ገንዘብ የሚቀበል ልጅ ከመካከላቸው ይመርጣሉ፡፡ ከዚያ በኋላ በየመንደሩ የዞሩ የባህል ዘፈን Eየዘፈኑና የሰጪዎችንም ስም Eያወደሱ ዳቦና ገንዘብ ይቀበላሉ፡፡ Eለቱ Eየጨፈሩ ካረፈዱ በኋላ ጨፍረው ያገኙትን ዳቦ ንድነት ተሰብስበው ይመገባሉ፡፡ ገንዘቡንም ተከፋፍለው ለየችግራቸው ያውሉታል፡፡ የቡሄ ወይንም የደብረ ታቦር በዓል የተወደደና በጣም የሚናፈቅ ነው፡፡ የደብረ ታቦር በዓል በኅብረተሰቡና በልጆች በኩል የሚታወቀው ቡሄ በሚል ስም ነው፡፡ ባቶች ቡሄ ማለት በራ፣ ብርሃን ማለት ነው ይላሉ፡፡ በደብረ ታቦር የበራውን ብርሃን ያመለክተናል፡፡
ወስብሐት ለእEግዚብሔር!

No comments:

Post a Comment