Thursday, August 15, 2013

የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በፈተና ውስጥ መሆኗን ክርስቲያኖች ገለጹ



  በኤርትራ የክርስቲያኖች መከራ ወደከፋ ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑን ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የኤርትራ ቤተክርስቲያን መሪዎች ኦፕን ዶርስ ኢንተርናሽናል ለተባለ የክርስቲያን ግብረ ሠናይ ድርጅት መናገራቸውን ዘኦርቶዶክስ ቸርች ዶት ኢንፎ የተባለ ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡ ከአዲቀዪ የሥነጥበብና ማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ 31 ተማሪዎችንና ከአስመራ ሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ተይዘው የተወሰዱትን አምስት ሰዎች ጨምሮ በዚህ ዓመት ብቻ በመንግስት ተይዘው የታሰሩት ክርስቲያኖች ቁጥር 191 መድረሱም ተመልክቷል፡፡
  ከዚህ ጋር በተያያዘ የኤርትራ መንግሥት ክርስቲያን የሆኑ እስከ ሦስት ሺሕ ሰዎችን እንዳሰረ የሚገመት ሲሆን ከነዚህ ውስጠ ፓትርያርኩ አቡነ አንቶኒዮስ ይገኙበታል፡፡ በዚህም ምክንያት የኤርትራኦ ርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አገልግሎት ከጊዜ ወደጊዜ እየተዳከመ ነው፡፡ በሰብአዊ መብት ጥሰት ዘወትር በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሪፖርት የሚወጣበት የኤርትራ መንግሥት ግን ክሶቹ ሁሉ መሠረተቢስና የተቀነባበሩ ናቸው ሲል ባገኘው አጋጣሚ መልስ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ በኤርትራ ግማሽ ያሁሉ ሕዝብ ክርስቲያን ሲሆን ከክርስቲያን ማኅበረሰቡ ደግሞ ከአሥሩ ዘጠኙ የኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት የሚከተሉ እንደሆነም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፡ ሐመር መጽሔት ሐምሌ 2005 ዓ.ም.

No comments:

Post a Comment