አሠርቱ ትእዛዛት - ስድስተኛው ትእዛዝ
1. ከአንድ በላይ ማግባት
በሐዲስ ኪዳን የተፈቀደው ሕግ
አንዲት ሚስት በአንድ ባል፣ አንድ ባልም በአንዲት ሚስት ጸንተው መኖራቸው ነው፡፡ ‹‹ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ
ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት።›› ቀዳ ቆሮ 7፡2፡፡
2. ከጋብቻ/ትዳር ውጪ
ፈቃደ ሥጋን መፈጸም
በጋብቻ/በትዳር አጋር ውጪ ፈቃደ
ሥጋን - ግኑኝነትን መፈጸም ዝሙት ነው፡፡
3. የቅርብ ዘመድ ማግባት
ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጪ ከቅርብ
ዘመድ ጋር የሚፈጸም ጋብቻ ዝሙት ነው፡፡ ‹‹ዮሐንስ ሄሮድስን። የወንድምህ ሚስት ለአንተ ልትሆን አልተፈቀደም ይለው ነበርና።››
ማር 6፡18፣ ‹‹ከእናንተም ማንም ሰው ኃፍረተ ሥጋውን ይገልጥ ዘንድ ወደ ዘመዱ ሁሉ አይቅረብ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።›› ዘሌዋ
18፡6፡፡ እንዳሉ፡፡ ይህ ዝምድናም መንፈሳዊ ዝምድናን (የክርስትና አባት/እናት ዝምድናን ይጨምራል፡፡)
4. በዝሙት የተፈታውን
ወይም የተፈታችውን ማግባት
በሞት ተለይቶ/ተለይታ ካልሆነ
በዝሙት የተፈታውን/ችውን ማግባት ዝሙት ነው፡፡ ‹‹እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ
ሁሉ ያመነዝራል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል አላቸው።›› ማቴ 19፡9፡፡
5. ምኞት
1. ከሰው ወገን ሌላውን ተገቢ ባልሆነ መንገድ መፈለግ ዝሙት ነው፡፡ ‹‹ወደ ሴት ያየ የተመኛትም
ሁሉ ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ
ጋር አመነዘረ፡፡›› ማቴ 5፡28፡፡
2. እግዚአብሔርን ትቶ ሌሎች አማልክትንም ማምለክ የቀናችውንም ሃይማኖት መተው ማመንዘር ነው፡፡
‹‹ሌሎች አማልክትን
ተከትለው አመነዘሩ ሰገዱላቸውም…›› መሳ 2፡17 እንደተባለ፡፡
ማመንዘር ከበድ ያለ ኃጢአት
ነው፡፡ ‹‹ከዝሙት ሽሹ፤ ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጪ ነው፡፡ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል፡፡››
ቀዳ ቆሮ 6፡18፡፡ እንደተባለ ዝሙት ነፍስንም ሆነ ሥጋን ስለሚያረክስ ነው፡፡ ቀዳ ቆሮ 6፡15-20፣ ዘፍጥ 6፣ ዘፍጥ 19፣
…፡፡ ወደ ክርስትና የተመለሱ አሕዛብ የተሠራላቸው ሕግም ከዝሙትና ከጣዖት አምልኮት እንዲርቁ የሚያሳስብ ነበር፡፡ የሐዋ 15፡19-20፡፡
ስለዚህ ለዝሙት ከሚያነሳሱ ምክንያቶች ሁሉ በመራቅ በጾምና በጸሎት በመወሰን ንስሐ እየገቡ ቅዱስ ቁርባን መቀበል በጽድቅ ታንጸን
እንድንኖር ይጠብቀናልና በተጠቀሱት መንፈሳዊ መንገዶች ተወስነን እንድንኖር እግዚአብሔር ይረዳን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡
ምንጭ:
-ሕግጋተ እግዚአብሔር ብፁዕ
ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ 3ኛ
/ ትርጉም ቀሲስ እሸቱ ታደሰ/
ማኅበረ ቅዱሳን 1995 ዓ.ም

No comments:
Post a Comment