በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ
ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
‹‹ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። ››
አንዳንዶች ይህን ሕግ ሲያነቡ ወይም ሲሰሙ የሚመለከታቸው ከሐድያን መናፍቃን ወይም ብዙ በመመራመር ወይም ከመፈላሰፍ የተነሳ ከሃይማኖት የወጡትን ነው ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም እኛ እንጾማለን፣ አሥራት እናወጣለን፣ ዘወትር እንጸልያለን፣ ከልባችን እንዘምራለን፣ በቤተ ክርስቲያን የጸሎት የአምልኮትና የመዝሙር መርሐ ግብሮችም ተሳትፎ እናደርጋለንና ትዕዛዙ እኛን አይመለከተንም ብለው የሚሠሩትን የሚታየውን ስለሚያስቡ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ይህ ትዕዛዝ ማንንም ሳይለይ ሁሉንም ሰው የሚመለከት ነው፡፡ ሌሎች አማልክት የተባሉትም ከድንጋይ ተጠርበው ከእንጨት ለዝበው የተሠሩትን ጣዖታት፣ በፀሐይ፣ በጨረቃ፣ በከዋክብት ማምለክን ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ሰው የሚያመልከውን የየራሱን ጣዖታት ናቸው፡፡

