“በአፄ ኃ/ሥላሴ የንግስና ዘመን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ መስቀል በያዘ አንበሳ አርማ የተዘጋጀ ነበረ፡፡
ይህም እስልምናውን ያገለለ ለአንድ ሃይማኖት ብቻ የቆመ አገዛዝ እንደነበረ የሚያረጋግጥ ነው፡፡”
በዚህ
ውይይት ላይ ከተለያዩ የመንግስት፣የሃይማኖትና ከአ.አ ዩኒቨርሲቲ የተወከሉ ተወያዮች ተሳትፈው ተመልክቻለሁ፡፡ የውይይቱ ዓላማ ለኔ
እንደገባኝ ሃይማኖትና መንግስት የተለያዩ ስለመሆናቸውና አንዱ በአንዱ ጣልቃ አይገባም የሚለውን የሕገ መንግስቱን አንቀፅ አፅንዖት
ለመስጠት ይምስለኛል፡፡
ውስጥ
ውስጡን ግን ነገር ያቆረ መስሎም ታየቶኛል፡፡ ምክንያቱም በቅርብ በተወካዮች ምክር ቤት ከተነሳው አክራሪነት ጉዳይ ጋር ተከታትሎ
መቅረቡ ነው፡፡ ይኸውም ምናልባት ያልገመትነውንና ያላሰብነውን ውሳኔ ያሰማናል የሚል ግምት አለኝ፡፡
በኢቴቪ
እየተደረገ ያለው ውይይት ስለ ሃይማኖቶች እኩልነት፣መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ ገብነት እንደማይኖር፣መንግስታዊ
ሃይማኖት መኖሩ ጉዳት እንዳለው ሊጠቁም ሞክሯል መርሃግብሩ፡፡ ከላይ በመግቢያዬ ላይ ከእስልምና ከተወከሉት ሌላ ከኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን፣ከካቶሊካዊት
ቤ/ክ፣ከወንጌላውያን ኅብረት እንዲሁም ከሰባተኛው ቀን አክባሪዎች የሃይማኖቱ ተወካዮች ተሳታፊች ናቸው፡፡ ሁሉም እውነት ነው ያሉትን
ጥቅሙንና ጉዳቱን በማንሳት ለማብራራት ሞክረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የእምነት ነፃነትን ለሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ያጎናፀፈው
መብት ነው፡፡ ይህ መብት ግን ሊተገበር የሚችለው አንዱ የአንዱን ሃይማኖት አክብሮና አስከብሮ ሲኖር ብቻ እንደሆነ ተሳታፊዎቹ አልዘነጉትም፡፡
በተግባር የመታየቱ ጉዳይ ግን አጠያያቂ ነው፡፡ ምክንያቱም እያየንና እየሰማን ያለነው ተቃራኒውን ስለሆነ፡፡
በየመሃሉ
ሲነሳ የነበረው ነጥብ በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርቲያን በቀደሙት ዘመናት ከነገስታቱ ልዩ ጥቅም የምታገኝ እነደነበረችና
ሌሎቹ ሃይማኖቶች ተገለው እነደነበር የሚያወሳ ነው፡፡ ከአንዱ ተሳታፊ በስተቀር የሁሉም ሃሳብ ይህንን ያጠናከረ ነበር፡፡ ሌሎቹ
ተሳታፊዎች ላይ ይታይ የነበረው ስሜት ግን ከንግግራቸውም የላቀ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
አሁን
ባለንበት ዘመናዊ ዓለም እንኳ ሳይቀር የመንግስት ሃይማኖት ያላቸው ሃገራት እንዳሉ የማይታበል ሃቅ ሆኖ እያለ ከተሳታፊዎቹ መካከል
መንግስትና ሃይማኖት መነጣጠል እንዳለባቸው ዓለማቀፍ ሕግ እንዳለ
ሲናገሩና ሌላውም ሲያጠናክሩት ለመታዘብ ችያለሁ፡፡ ለዚህ ምክንያታቸው ማጠናከሪያ ያስቀመጡት ዋና ነጥብ መንግስታዊ ሃይማኖት መኖሩ
ለዴሞክራሲው ግንባታ እንቅፋት ይሆናል ነው፡፡
እኔም
ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ ስነሳ መንግስታዊ ሃይማኖት ይኑር የሚል ሃሳብ አንግቤ አይደለም፡፡ ነገር ግን የሚቆጨኝ ሰዎች ባገኙት እድልና
አጋጣሚ ሁሉ /የሌላ እምነት ተከታዮች/ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ለመኮነን እና ለማጣጣል ሲሞክሩ ማየቴና መስማቴ ነው፡፡ ይህች
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እንደበደለቻቸው፣እንዳፈነቻቸው፣በነፃነት እንዳያስተምሩና እምነቶቻቸውን እንዳያስፋፉ አድርጋቸው እንደቆየችና
አሁን ሕገ መንግስቱ ነፃነት እንደሰጣቸው ሲደሰኩሩ መስማት የተለመደ ሆኗል፡፡ በተክርስቲያኗን ሳያነሱ ሕገ መንግስቱ ስለሰጣቸው
ነፃነት ማውራት አይችሉምን? በርግጥ ይችላሉ፡፡
ነገር
ግን ያልጠገገ የክፋትና የቅናት ቁስል ስላለባቸው ይቆጠቁጣቸዋል፡፡ ስለዚህ ባገኙት አጋጣሚ ብሶት የመሰለ ጥላቻቸውን ያንፀባርቃሉ፡፡
በውይይቱም ላይ ያየሁት ይህንኑ ነው፡፡ ከ 338 ዓ.ም ጀምሮ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርቲያን ብሔራዊ ሃይማኖት ነበረች እስከ ደርግ መምጫ
ድረስ፡፡ ዶ/ር አባ ኃ/ማርያም በውይይቱ ላይ እነደተናገሩት የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርቲያን ብሔራዊ ሃይማኖት ብትሆን ቢያንሳት እነጂ የሚበዛባት
አይሆንም፡፡ ለምን ቢሉ ኢትዮጵያና ቤተክርስቲያኒቱ የአንድ ሳንቲም ሁለት ፊት ስለሆኑ፡፡
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርቲያን
ለኢትዮጵያ የዋለቻቸው ውለታዎች እንዲህ በቀላሉ በኔ ሊነገሩ የሚችሉ አይደሉም ቀለም በጥብጣ፣ፊደል ቀርጻ፣የዘመን መቁጠሪያን ቀምራ፣ዜማን
ከነምልክቱ አበርክታለች፡፡ እንዲሁም ሥነ ሕንፃንና ሥነ ጽሑፍን ለልጆቿ እነሆኝ ብላለች፡፡ ስለዚህ ይህች ስንዱ እመቤት ብሔራዊት
ብትባል ምን ይደንቃል? ለሃገሪቱ ያበረከተቻቸው እጅግ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ሥነ ምግባርንና ግብረ ገብነትን አስተምራለች በትውልዱ
ውስጥም አስርጻለች፡፡ ከሁሉም በላይ ዛሬ ያለንባት ብርቅዬ ሀገር ከነ ባህሏ፣ታሪኳና እምነቷ ከውስጥም ከውጭም ጠላቶች አቅባ አስረክባናለች፡፡
አሁን
የኢትዮጵያ እየተባሉ የሚጠሩት የሃይማኖት ድርጅቶች በሙሉ ለኢትዮጵያ
ምን አበርክተዋል ቢባል ምንም ነው፡፡ እነርሱም ልቡናቸው ያውቀዋል፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ክ የምትቀድሰው ቅዳሴ፣የምታዜመው
ዜማ፣የምትወርበው ወረብ ወዘተርፈ የት መጣውን ብትጠይቋት መልሷ ከኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሰርቄ እነደምትል ጥርጥር የለኝም
ያውም ከነባለሙያው፡፡ ይህ ደግሞ ሌላው ዓለም ላይ እንዳደረገችው ሁሉ እኛም ጋር ለመመሳሰል የተጠበበችበት ነው፡፡
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን
ለኢትዮጵያ ብኵርናዋ ናት፡፡ ይህንን ብኵርናዋን ልትጠብቀው ይገባታል፡፡ ይህች ቤተክርስቲያን የማንንም አልቀማችም ከሷም እንድትነጠቅ
አትፈልግም፡፡ ማንንም ጠብ የለሽ በዳቦ ብላ አታውቅም፡፡ ሌሎችም እንዲህ እንዲያደርጉባት አትፈቅድም፡፡ ዋናው ነገር ኢትዮጵያ በቀደሙት
ዘመናት በሰንደቋ ላይ የመስቀል ምልክት የማኖሯ ጉዳይ ሳይሆን ሌሎቹንም ሃይማኖቶች እኩል መብት ሰጥታ እንዲደራጁ መፍቀዷንም ማሰብና
ማስታወስ ግድ ይላል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከዘመነ ደርገ ውጪ ሁሉም መንግስታት/ነገሥታት/ በተለይም ለእስልምናው ቦታ የነሱበት ሁኔታ
አልነበረም፡፡ ደርግ ደግሞ አለየም ሁሉንም እኩል መብታቸውን ነጥቋቸዋል፡፡ መቼም ኢትዮጵያ ከውጭ ጠላቶቿ ጋር ስትዋጋ ሙስሊም አርበኞች
አልነበሩም ማለት አንችልም፡፡ በርግጠኝነት አሉ፡፡ ሙስሊሙና ክርስቲያኑ ኢትዮጵያዊ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሁሉም የኑሮ ጉዞ ውስጥ
እኩል ተሳታፊ ነበሩ፡፡ ወደዚህ ግን ከእድር፣ ከትምህርት ቤት፣ ከተለያዩ ማህበራዊ ተሳትፎዎች ራሳቸውን አገለሉ፡፡ ማንም ሳይላቸው
በራሳቸው ጊዜ፡፡ ከውጭ ሰርፆ የገባው አባዜ በማኅበራዊ ኑሮው ላይ ጭነቱን ጫነ፡፡ ከዛም መለያየቱ በዛ፡፡ ይህ ቢሆንም ሕገ መንግስቱ
ያጎናፀፋቸው መብት ስለሆነ ምንም አላልንም፡፡ መብታቸው ነው፤ ሕገ መንግስታዊ፡፡ ይሄን ስል ግን ሁሉም አይደሉም፡፡ ኢትዮጵያውያኑ
ሙስሊሞች ዛሬም እንደጥንቱ ናቸው፡፡
ሌሎቹ
ግን ውጭ ሃገር ባሉ የእምነቱ አራማጆች ተሰብከውና ተጽፈው የተሰራጩትን የማኅበረሰቡን አኗኗር ሳያገናዝቡ እንደወረደ በመተርጎም
እምነታችንና የእምነት መሰረታችንን ሲነቅፉና ሲሳደቡ ይስተዋላሉ፡፡ ይህም አልበቃ ብሏችው ምናመልክበት ድረስ መጥተው አረዱን አቃጠሉን፡፡
ምንም አላልን ዝም ብቻ፡፡ መቻቻል አይደል ቻልነው፡፡ ጅሃድ ሲታወጅብን ዝም ስላልን የክርስቲያኑ ስም ካልተጠራ እንደህመም ስለሚቆጠር
አንዳንድ…ተብለን እንጨመራለን፡፡
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን
ሕዝቡን በአንድ ገምዳ ያስተሳሰረች፣አንድነትን ከመለያየት አልቃ የሰበከች፣ከሁሉም ኢትዮጵያዊነት ይበልጣል እያለች ዘወትር ያለመታከት
የምታስታውስ ናት፡፡ ቅርሶቿን በጉያዋ ደብቃ ከእሳትና ከአጥፊዎች ጠብቃ አቆይታለች፡፡
ታድያ
ስለምን ውለታዋ ተዘንግቶ እንደ ጨቋኝ ትቆጠራለች ለባሕሪዋ አይስማማም፡፡ ኢትዮጵያ ከማናቸውም ሀገር ቀድማ በ34 ዓ.ም በነገሥታቶቿ
በጃንደረባው አማካኝነት ክርስትናን ተቀብላለች፡፡ ይህች ሃይማኖት የሕዝቡ በቻም ሳትሆን የነገሥታቱም እምነት ነበረች፡፡ አሁን ግን
አይደለችም፡፡ ቢሆንም አንከፋም፡፡ ነገር ግን በክፉ ዓይን መታየቷ ይቁም፡፡ በሩሲያ ፕሬዚዳንቱ፣ጠቅላይ ሚኒስትሩና ባለቤቶቻቸው
የፋሲካን በአል በቤተ መቅደስ ተገኝተው ሲያከብሩ ሲታይ ምንኛ ያስቀናል፡፡ እኛ ወደኋላ እነርሱ ወደፊት፡፡ እኛ ሃይማኖት ያለው
መንግስት የለንም፡፡ ምክንያቱም ሌሎቹ ይቀየማሉና፡፡ እስካሁን በየትኛውም አጋጣሚ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን እምነት ተከታይ ነኝ የሚል ባለስልጣን አላጋጠመኝም፡፡ በግልባጩ የፕሮቴስታንትና
የእስልምና ተከታዮች የሆኑት ግን በይፋ በቃለ መጠይቃቸው መሃል ሲናገሩ ብዙ ጊዜ አጋጥሞኛል፡፡ በሚኒስትር ደረጃ፡፡
የሆነ
ሆኖ ይህች ጥንታዊት ቤተክርስቲያን በዚች ጥንታዊት ሀገር ላይ ለሰላም መስፈንና አብሮ የመኖር መቻቻልና ለመልካም አስተዳደር ግንባታ ኃላፊነት አለባት፡፡ ይህ ሲባል የቤተክርስቲያኒቱንና የሀገሪቱን
ታሪካዊ ቁርኝት መሰረት በማድረግ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ኢትዮጵያና የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርቲያን
ተነጣጥለው ሊታዩ አይችሉምና፡፡
የኢትዮጵያ
ዕሴት፣ ባህላዊና ታሪካዊ ምንነት በአዛኛው ከቤተክርስቲያኒቱ ጋር
የተቆራኘ ስለመሆኑ ብዙ አስረጂ አያስፈገውም፡፡ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርቲያን
የኢትዮጵያውያን ቅርስ የሆኑትን የመንፈሳዊ ትምህርት፣የዝማሬ፣የቅኔ፣ይፍትሐ ነግሥት፣የፊደል፣የዘመን አቆጣጠር የመሳሰሉትን ሥርዓተ
እውቀቶች ምንጭና ባለቤት መሆንዋ በኢትዮጵያውያን የዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ግዘፍ ነሶ የሚታይ ሃቅ ነው፡፡ ይህች ቤተክርስቲያን
የኢትዮጵያውያን ጥንታዊ ሥልጣኔ ክብር የተላበሰች፣የሀገሪቱን ውርደትና ውድቀት፣ብልፅግናዋንና ዕድገቷን የተጋራች ከመከራዋም የተቋደሰች
ናት፡፡ የቤተክርስቲያኒቱን ቀደምት አበው ታሪክና ገድል በክብር ጠብቃ ለተተኪው ትውልድ ልታሸጋግር የምትችለው ከወቅቱ ጋር መግባባት
ስትችልና የእምነት መሰረቶቿን ለመጠበቅ የሚረዳ ብልሃትና ስልት ስታበጅ፤ከሁሉም በላይ የውስጥ አንድነቷን ስታጠናክር መሆኑ ሊዘነጋ
አይገባውም፡፡
ይህም
ይሳካ ዘንድ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶችና አገልጋዮች በሙሉ ስለ ማህበራዊ ሰላምና ስለ መልካም አስተዳደር የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው
ከየዕለት ተግባሮቻቸው ጋርም እነዚህ ዕሴቶች እንዲዋሃዱ ማድረግ እጅግ ወሳኝ ነጥብ ነው፡፡ “ወደምትገቡበት ቤት ሁሉ አስቀድማችሁ ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን በሉ፡፡”
ሉቃስ 10፣5፡፡ እኛ የሰላም አምላክ ነውና ያለን ሰላምን እንሰብካለን፡፡ እርሱ ስለዓለም ሲል አንድያ ልጁን ለመስጠት አልራራም፡፡ዮሐ
3፣16፡፡ ይህም ፍቅር ነው ፡፡ ኦርቶዶእሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም ስብከቷም ትምህርቷም ከዚህ የወጣ አይደለም፡፡ ያለሰላም
እግዚአብሔርን ማየት የሚችል የለምና፡፡ ዕብ 12፣14፡፡
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ይጠብቅ አሜን፡፡
Amen Bless u
ReplyDelete