ገና
የኔ ቢጤ ከእንቅልፉ ሳይነቃ የአቃቂ ቅጥቅጥ ቼንቶዎችና ረዳቶቻቸው በአንድነት የተኛውን ለማንቃት በሚመስል ሁኔታ ጩኸታቸውን ይለቁታል፡፡
ቼንቶዎቹ በጡሩምባቸው፣ረዳቶቹ በአፋቸው፡፡ ጳራም… ጳራም… ጳራም… አዲሳባ… አዲሳባ… ሳሪስ አቦ ለገሃር፡፡ እነኚህ በራሪዎቹ ናቸው፡፡
በአንፃሩ ፈጣን ናቸው፡፡ ምክንያቱም መንገድ ሳይዘጋጋ በየቦታው ሳይገተሩ ስለሚሄዱ ነው፡፡ ከጠዋቱ 1ሰዓት ጀምሮ የሚገኙቱ ደግሞ
በፍጥነታቸው ከኤሊ የሚሻሉት ሞተርና ጎማ ስላላቸው ብቻ ነው፡፡ ከሚሄዱት ፍጥነት በላይ የሞተራቸውና የረዳቶቻቸው ጩኸት ናላ ያናጋል፡፡
“እዛ ጋር ጠጋ በል” “አንተ
ብረት ተደግፈህ የቆምከው ወይ እለፍ ወይ ሰው አሳልፍ” “አንቺ ደግሞ በጎን ገባ በይ”… ሞላ አያውቁም ሰው ካገኙ እንደ ዱቄት ይጠቀጥቃሉ፤ያጭቃሉም፡፡
በነዚህ
መኪኖች አዘውትሮ እንደኔ ተጓዥ የሆነ ሰው አፍ አውጥቶ ባይጸልይም በልቡ ግን “ማርያም
ማርያም” ማለቱ አይቀርም፡፡ ለምን
ቢሉ ረዳቱ ከመኪናው ፍጥነት በተሻለ ሒሳቡን ከሰበሰበ በግማሽ ሰከንድ ልዩነት አጉል ቦታ መኪናው ቀጥ ሊል ይችላልና ነው፡፡ ለምን
ቀጥ ይላል? ነዳጅ ጨርሶ አልያም ችንጋ ተፈቶ ነው፡፡ ጠዋት መሆኑን
ልብ ይሏል ታድያ፡፡ በዚህም ተገልጋዩ ይበሳጫል፡፡ ለገንዘቡ እንዳይምስላችሁ የሚበሳጨው ሌላ አማራጭ ትራንስፖርት የማይገኝበት ቦታ
ለመውረድ ስለሚገደድ እንጂ፡፡ ከጉዳዩ መስተጓጎሉ ደግሞ ይብሳል፡፡
